የወ/ሮ ስኂን ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2017 ዓ.ም ለትምህርትና ስልጠና እንዲሁም ለቢሮዎች አገልግሎት የሚውል ጥሬ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Woizero Siheen Polytechnic College (ወ/ሮ ስኂን ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የወ/ሮ ስኂን ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2017 ዓ.ም ለትምህርትና ስልጠና እንዲሁም ለቢሮዎች አገልግሎት የሚውል
- የህንፃ መሳሪያና የቧንቧ እቃዎች፣
- የአውቶ እቃዎች፣
- የጽዳት እቃዎች፣
- የሆቴልና ቱሪዝም ዕቃዎች፣
- የኤሌክትሪክ እቃዎች፣
- የኮምፒዩተር ተዛማጅ እቃዎች፣
- የጽህፈት መሳሪያዎች፣
- ለከተማ ግብርና ስልጠና ዘርፍ አገልግሎት የሚውሉ ጥሬ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ከዚህ በታች መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመግዛት መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና በንግድ ዘርፉ የተሰማሩ፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፤
- የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለሚሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1- 4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙትን የእቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን /ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከወ/ሮ ስኂን ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 204 /አዲሱ ህንፃ / ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ የከፈሉበትን ማስረጃ መያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ መክፈቻ ዕለት ኦሪጅናል ንግድ ፈቃድና ቫት ሰርተፊኬት የግብር መክፈያ የግብር ክፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ሲጠየቁ ማሳየት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሞልተው በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናልና ኮፒ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ በወ/ሮ ስኂን ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 204/አዲሱ ህንፃ /በመገኘት የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚችሉ ሲሆን በቀጣዩ ቀን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሰነዱን በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
- ሳጥኑም በዚህ ሰዓት ይታሸጋል በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚዘጋውና የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 204 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033-111-10-10 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፣
የወ/ሮ ስኂን ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ የሥራ ሂደት
