የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለበረራ መስተንግዶ (onboard service) እና ለስካይላይት ሆቴል አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የታሸገ ውሀ (Spring or Purified Bottled Water) አቅራቢ ድርጅቶችን አወዳድሮ የሦስት (3) ዓመት ውል በመግባት አብሮ ለመስራት ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር :- SSNT-T519
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለበረራ መስተንግዶ (onboard service) እና ለስካይላይት ሆቴል አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የታሸገ ውሀ (Spring or Purified Bottled Water) አቅራቢ ድርጅቶችን አወዳድሮ የሦስት (3) ዓመት ውል በመግባት አብሮ ለመስራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟላ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡-
- በአገልግሎቱ ዘርፍ ለመሠማራት ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፤ ለ2017 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና የTIN ምዝገባ ወረቀት ያለው፣ VAT ተመዝጋቢ የሆነ፣ ሦስት (3) ዓመት እና ከዚያ በላይ የሥራ ልምድ ያለው ተጫራች በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ሁለት መቶ ብር (ብር 200.00) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T519 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ቅጂውን (Scan copy) በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
- በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት አምስት መቶ ሺህ ብር (500,000.00 ብር) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ እና ውስንነት ያለው (Conditional) የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂከ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ :-
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል
ስልክ ቁጥር: 011-517-8953
ኢ-ሜይል: TeymeT@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
