የአዳማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ለ2017 የበጀት አመት ምግብ እና መኝታ አገልግሎት የሚሰጡ ህጋዊ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
Adama City Football Club (የአዳማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዳማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ለ2017 የበጀት አመት ምግብ እና መኝታ አገልግሎት የሚሰጡ ህጋዊ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
ተወዳዳሪዎች ሟሟላት ያለባቸው መስፈርቶች /የተጫራቾች መመሪያ/::
-
- ማንኛውም ድርጅት ግለሰብ እና በዘርፉ የተሰማሩ ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው የዘመኑን ግብር የገበረ እና ማሰረጃ ማቅረብ የሚችል፤
- ተጫራቾች ቫት ተመዝጋቢ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 በመክፈል አዳማ ከተማ መዘጋጃ ቤት ሲንቄ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1054551161211 በማስገባት ጨረታው ከወጣት የስራ ቀን ጀምሮ አዳማ ከተማ እግር ኳስ ጽ/ቤት መግዛት ይችላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ምግብ እና መኝታ አቅርቦት 50,000.00 /ሃምሳ ሺ/ ብር በባንክ ቼክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ባይገኙም ጨረታው አይስተጓጎልም፡፡ ሆኖም 11ኛው ቀን በዓል ወይም የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በታሸገ ኤንቨሎፕ ኮፒውን እና ኦርጅናሉን በተናጠል በማቅረብ አዳማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ቤት በመቅረብ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ቀን ማስገባት ይችላሉ፡፡
- የምግብ ዝግጅት ቦታ ለስፖርታኛ ምግብ በሚዘጋጅበት አዳራሽ ውስጥ ከአልኮል መጠጥ፣ ከተለያዩ ሱስ አስያዥ ዕፆች፤ ጭፈራ ቤት እንዲሁም ስፖርተኛን ሊረብሹ የሚችሉ የፋብሪካ ድምፅ የራቀ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች በቂ የማድቤት እና የምግብ ቁሳቁስ ከበቂ የሰው ሃይል ጋር ያለው መሆን ይጠበቅበታል።
- ተጫራቾች በ2016 ዓ.ም በዚህ የስራ ዘርፍ ተሰማርተው እየሰሩ ያሉ መሆኑን የሚገልፅ የስራ ልምድ ከንግድ እና ገበያ አገልግሎት ጽ/ቤት እና ሲሰሩ ከነበሩበት ቦታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- መስሪያቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፊልም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የአዳማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ
