የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2017 በጀት የኮርፖሬሽኑ ሎጎ የታተመበት የእጅ ቦርሳ እና እስክርቢቶ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው መስፈርት መሰረት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን)
ኮርፖሬሽኑ ለስጦታ የሚሆን የእጅ ቦርሳ እና እስክርቢቶ
ለመግዛት የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢ.ግ.ሥ.ኮ./ብግጨ/11/2017
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2017 በጀት የኮርፖሬሽኑ ሎጎ የታተመበት የእጅ ቦርሳ እና እስክርቢቶ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው መስፈርት መሰረት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የቫት ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ የምዝገባ ሠርተፊኬት (TIN) እንዲሁም ከገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳሪስ አቦ ፋፋ የምግብ አ.ማ አጠገብ የቀድሞው እርሻ መሣሪያዎችና ቴክኒክ አገልግሎት አ.ማ ግቢ የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 110 ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ። ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አሥር ሺህ ብር ብቻ) በሲ.ፒ.ኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ (Unconditional) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታው ዋጋ ለ60 ቀናት የፀና ይሆናል።
ጨረታው ጥር 8 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ የቴክኒካል ጨረታ ሰነድ የመክፈቻ ስነሥርዓት ይከናወናል፡፡
ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ ፡-
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
ስልክ 011 470-90-95/0114-423 608
ፋክስ 0114-421 312
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
