የአዲስ አበባ ተግባር ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2017 በጀት አመት የሁለተኛ ዙር ግልፅ ጨረታ በመደበኛ አላቂ፣ እና ቋሚ እቃዎች እንዲሁም የስልጠና እና የቢሮ እቃዎች የሰራተኞች ጥቅማ ጥቅሞች አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን በማወዳደር ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
A.A. TEGBARE-ID POLYTECHNIC COLLEGE (የአዲስ አበባ ተግባር ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ተግባር ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2017 በጀት አመት የሁለተኛ ዙር ግልፅ ጨረታ በመደበኛ አላቂ፣ እና ቋሚ እቃዎች እንዲሁም የስልጠና እና የቢሮ እቃዎች የሰራተኞች ጥቅማ ጥቅሞች አገልግሎት የሚውሉ፡-
ሎት 1 ፤ የሰራተኞች ጥቅማ ጥቅሞች - 10,000 ብር
ሎት 2 ፤ አላቂ የቢሮ እቃዎች - 10,000 ብር
ሎት 3 ፤ የአይ.ሲ.ቲ ዲፓርትመንት የስልጠና እቃዎች - 30,000 ብር
ሎት 4 ፤ የሰርቬይንግ እና ድራፍቲንግ የስልጠና እቃዎች - 2,000 ብር
ሎት 5 ፤ የኤሌክትሪክ ኤሌክትሮኒክስ የስልጠና እቃዎች - 30,000 ብር
ሎት 6 ፧ የኮንስትራክሽን ዲፓርትመንት የስልጠና እቃዎች - 30,000 ብር
ሎት 7 ፤ የአዉቶሞቲቭ ዲፓርትመንት የስልጠና እቃዎች - 50,000 ብር
ሎት 8 ፤ የማኑፋክቸሪንግ ዲፓርትመንት የስልጠና እቃዎች - 50,000 ብር
ሎት 9 ፤ የጋርመንት ቴክስታይል ዲፓርትመንት የስልጠና እቃዎች - 30,000 ብር
ሎት 10 ፤ የባዮሜዲካል ዲፓርትመንት የስልጠና እቃዎች - 10,000 ብር
ሎት 11 ፤ የፈርኒቸር ሜኪንግ ዲፓርትመንት የስልጠና እቃዎች - 50,000 ብር
ሎት 12 ፤ ህንፃ አስተዳደር እቃዎች - 30,000 ብር
በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን በማወዳደር ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስፈልጋቸውን ህጋዊ ሰነዶቻቸውን ከላይ በተጠቀሰውና ተዛማጅ የንግድ ዘርፎች
የተሰማሩ መሆን የሚገባቸው ሆነው አቅራቢዎች ፦
ሀ. ህጋዊ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ
ለ. የግብር ከፋይነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት (TIN)
ሐ. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ
መ. በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች ከታች በተገለፀው አድራሻ በኮሌጁ ክፍያ እና ሂሳብ ዳይሬክቶሬት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በስራ ሰዓት ግዥ እቅድ አፈፃፀም ዳይሮክቶሬት ቢሮ ቁጥር 14 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- በሁሉም ሎቶች ለተጠቀሱት ግብአቶች አንድ የፋይናንሻል ኦርጅናል እና አንድ የፋይናንሻል ሰነድ ኮፒ እንዲሁም አንድ ቴክኒካል ኦርጂናል እና አንድ ቴክኒካል ኮፒ ለየብቻ በማሸግ በተጠቀሰው የግዥ ጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አባሪ አድርገው የተጠየቁትን ማስረጃዎች በሟሟላት የድርጅቱ ማህተምና ፈርማ በሁሉም ገፆች ላይ በማኖር ለፋይናንስ መወዳደሪያ አርጅናልና ኮፒ ለየብቻው በማድረግ የታሸጉ ፖስታዎችን መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡
- በሁሉም ሎቶች በተጠቀሱት ግብአቶች ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንከ የተረጋገጠ CPO ወይም ካሽ በአዲስ አበባ ተግባር ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስም አዘጋጅተው ወይንም በጥሬ ገንዘብ ለኮሌጅ ክፍያና ሂሳብ በመክፈል ከጨረታ ሰነዱ ጋር አባሪ አድርገው በተሰጠው ስፔስፊኬሽን ላይ በመሙላትና የድርጅቱን ማህተም እና ፊርማ በሁሉም ገጾች ላይ በማኖር ኦርጅናል እና ኮፒ ፖስታዎችን ታሸጎ በተለያዩ ፖስታ በማድረግ መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን ዝርዝር ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ 11ኛው ቀን (አስራ አንደኛው) ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በአዲስ አበባ ተግባር ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 14 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ 4፡00 ሰአት ታሽጎ በ4፡30 በአዲስ አበባ ተግባር ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በትልቁ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል፡፡
- ለተሸናፊ ተጫራቾች (CPO) ሲፒኦ ተመላሽ የሚደረገው ኮሌጁ አሸናፊውን ተጫራቾች ለይቶ በማስታወቂያ ካሳወቀ እና ውል ካስገባ በኋላ ይሆናል፡፡
- ለአሸናፊ ተጫራቾች (CPO) ሲፒኦ ተመላሽ የሚደረገው ከኮሌጁ ጋር የአቅርቦት ውል ከፈፀሙና እቃዎች ካቀረቡ በኋላ ነው፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጮች ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በተጠቀሱት ሎቶች ናሙና የሚጠይቁ ናሙና ማቅረብ እንዲሁም ቴክኒካል ዶክመንት የሚጠይቁ ቴክኒካል ዶክመንት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በአራት ፖስታ ማለትም አንድ ኦርጂናል ፋይናንሻል፣ አንድ ኮፒ ፋይናንሻል እንዲሁም አንድ ኦርጂናል ቴክኒካል እና አንድ ኮፒ ቴክኒካል ለየብቻው አሽጋችሁ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ቴክኒካል ዶክመንት ወይም ሳምፕል ለተጠየቁ ግብዓቶች ሳምፕል እና ቴክኒካል ዶክመንት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ዋጋ የሚሞላው ኮሌጁ በሰጠው የዋጋ መሙያ ብቻ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ ፡- ስልክ ቁጥር 0115512562 ደውለው መረዳት ይችላሉ
የአዲስ አበባ ተግባር ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
አድራሻ ፡- ሜክሲኮ አደባባይ ከፌዴራል ፖሊስ ፊት ለፊት
የአዲስ አበባ ተግባር ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
