የከሚሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በ2017 በጀት ዓመት ለኮሌጁ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የጽሕፈት መሳሪያዎችን፣ አላቂ የጽዳት ዕቃዎችን ፤ የትምህርት መረጃ ዕቃዎችን፣ የሰራተኞች ደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡
Kamise College of Teachers Education (የከሚሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የከሚሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በ2017 በጀት ዓመት ለኮሌጁ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የጽሕፈት መሳሪያዎችን፣ አላቂ የጽዳት ዕቃዎችን ፤ የትምህርት መረጃ ዕቃዎችን፣ የሰራተኞች ደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡
ስለዚህ በዘርፉ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን ነምበር/ ያላቸው::
- የግዥ መጠኑ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁ.1 እስከ 3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ኦርጅናልና ኮፒ አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከላይ የተጠቀሱትን የዕቃ አይነቶች ዝርዝር የጨረታ ሰነድ መግለጫ /Specification/ ብር 30.00 /ሰላሳ/ ለእያንዳንዱ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 21 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የሚቀርቡ እቃዎች በሙሉ ኦርጅናልና ኮሌጁን ለሌላ ኪሳራ የማይዳርጉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ 1% ቢድ ቦንድ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሃሳባቸውን ኦርጅናል እና ኮፒ በመለየት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን ድረስ በኮሌጁ ግዥ ፋይ/ን/አስ/ቢሮ ቁጥር 21 ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በሚቆጠር በ21ኛው ቀን ማለትም በኮሌጁ ግዥ ፋይ/ቢሮ ቁጥር 21 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊዎች ማሸነፋቸው በደብዳቤ እንደተገለጸላቸው 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ መፈጸም አለባቸው፡፡
- አሽናፊው ተጫራች የሚያቀርባቸው እቃዎች ለኮሌጁ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0338540037 ላይ በመደወል መረዳት ይችላሉ፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የከሚሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ
