በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ ቻግኒ ቅ/ጽ/ቤት የሚገኝ 5ኛ ደረጃ የዕጣን ምርት ብዛት 240 ኩንታል ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን)
የዕጣን ምርት ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢግስኮ - ኢምዘደውአዘ/ግጨ /ሽ01/2017
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ ቻግኒ ቅ/ጽ/ቤት የሚገኝ 5ኛ ደረጃ የዕጣን ምርት ብዛት 240 ኩንታል ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ሁሉ በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክርነት ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ የምስክርነት ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የምስክርነት ወረቀት (ክሊራንስ) ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት እና ከ7፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት አዲስ አበባ በሚገኘው በዘርፍ ጽ/ቤት ቃሊቲ ጉምሩክ ፊት ለፊት የኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4 እና የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ከ2% ያላነሰ በCPO በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ ስም ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል የጨረታው ዋጋ ለ 60 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል።
- ማንኛውም ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የሚጠይቀውን በሙሉ አሟልቶ ማቅረብ ይጠበቅበታል። የዕጣን ምርት ሽያጭ ተጫራቹ በሚሰጠው ዋጋ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይጨመራል።
- ጨረታው ጥር 08 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ጥር 08 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዘርፉ ቢሮ ቁጥር 4 ይከፈታል።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የቀረበው የዕጣን ምርት መጫረት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
- ዘርፉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ 011 6 18 61 25
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
የኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ
