አጋርፋ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ 2016/17 ያመረተዉን 3ኛ ደረጃ ዛላ በርበሬ 17.48 ኩንታል እና በ2017/2018 3ኛ ደረጃ ዛላ በርበሬ 25.49 (ሀያ አምስት ኩንታል ከ49/100 በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
Agarfa Agricultural Technical Vocational Educational & Training College (አጋርፋ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ)
የምርት ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የሽያጭ መለያ ቁጥር 07/002/2019 ዓ.ም
አጋርፋ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ 2016/17 ያመረተዉን 3ኛ ደረጃ ዛላ በርበሬ 17.48 ኩንታል እና በ2017/2018 3ኛ ደረጃ ዛላ በርበሬ 25.49 (ሀያ አምስት ኩንታል ከ49/100)፣ አዶሻ ገብስ 380(ሶስት መቶ ሰማንያ ኩንታል)፣ ኪንግ በርድ ስንዴ 82(ሰማንያ ሁለት ኩንታል)፣ ትራቭለር ገብስ 200(ሁለት መቶ ኩንታል)፣ ኢቦኒ ገብስ 317(ሶስት መቶ አስራ ሰባት ኩንታል)፣ ሄነሪኬ ገብስ 24(ሀያ አራት ኩንታል)፣ አናሶ ገብስ 16(አስራ ስድስት ኩንታል) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለጹትን መመሪያዎች እና ግዴታዎችን በማሟላት መወዳደር ይችላሉ::
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከመስኩ ጋር አግባብነት ያለው የታደሰ/የእድሳት ጊዜው ያላለፈበት የሥራ ንግድ ፍቃድ፣ ጊዜው ያላለፈበት የድጋፍ ደብዳቤ/የምስክር ወረቀት/ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት ምርት የሰጠውን ጠቅ/ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ እና የዋስትና ገዜወ ከ2(ሁለት)ወር ያላነሰ የባንክ ዋስትና /CPO/ በኮሌጁ በአጋርፋ የግብርና ቴክኒክ የትምህርት ስልጠና ኮሌጅ ስም በማዘጋጀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለጸለት በ5 (አምስት )ቀናት ወስጥ የውል ስምምነት ካልፈጸመ ፍቃደኛ እንዳልሆነ ተቆጥሮ ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለኮሌጁ ገቢ ይሆናል::
- የተዘጋጀውን የመጫረቻ ሰነድ ከአ/ግ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ ከግዥና ፋይናንስ ቢሮ እና አዲስ አበባ ሀይሌ ገ/ስላሴ ጎዳና በጌታነህ በሻህ ህንጻ በኩል ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ አዲስ ህይወት ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው አ/ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥልጠና ኮሌጅ ጉዳይ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ከሚገኘው የአጋርፋ ኮሌጅ ጉዳይ አስፈጻሚ ጽ/ቤት በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 200 ( ሁለት መቶ) ብር በስራ ቀናት መግዛት ይችላሉ::
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10(አስር) የስራ ቀናት ውሥጥ መግዛት ይቻላል፣ እንዲሁም የዋጋ ማቅረቢያቸውን ኦርጂናሉንና ኮፒዉን በመለየት አስፈላጊ ከሆኑ ከተያያዥ የጨረታ ሰነዶች ጋር በፖስታ ውስጥ በማሸግ ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሣጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል::
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ቀናት እስከ መዝጊያው ቀን ድረስ መግዛት ይቻላል፣ እንዲሁም የዋጋ ማቅረቢያቸውን ኦርጂናሉንና ኮፒዉን በመለየት አስፈላጊ ከሆኑ ከተያያዥ የጨረታ ሰነዶች ጋር በፖስታ ውስጥ በማሸግ ከፍ ብሎ በተጠቀሰዉ አድራሻ አዲስ አበባ የኮሌጁ ጉዳይ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሣጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- የጨረታው መክፈቻ ቀን እንደ አጋጣሚ ሆኖ ብሄራዊ በዓል ላይ የሚውል ከሆነ ጨረታው በቀጣይ የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይከፈታል እንዲሁም ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት ተቀባይነት የለውም በተጨማሪም ኮሌጁ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- የምርቱን ናሙና ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ባሌ አጋርፋ የግብርና ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ አጋርፋ ቀርበው ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ በኮሌጁ አህል መጋዘን ማየት ይችላሉ::
- ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 0116625004 አዲስ አበባ ወይም 0911490870፣0930108007 እና 0922319274 አጋርፋ የግ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ ደውለዉ መጠቀም ይችላሉ::
አጋርፋ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ
✨ messages.ai_summary
Agarfa Agricultural TVET College invites bids for the sale of third-grade shallot pepper, Adosha barley, King Bird wheat, Traveler barley, Ebony barley, Henrique barley, and Anaso barley. Bidders must submit a valid business license and clearance. Samples can be viewed at the college.
