Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኛ ሴቶች ብሔራዊ ማኅበር
  • Address የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ሚናሮል ጀርባ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0911-115157
  • Website
  • Deadline02 Oct 2026, 4:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን ጋዜጣ
  • Bid Document Priceብር 200.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityጠቅላላ ዋጋ 2ዐ በመቶ (20%) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ
  • opening dateበዚያው ቀን ከቀኑ 10፡30 ሠዓት
  • Categories Furniture And Furnishing , Office And Home Furniture , Other Sales

የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ሲገለገልባቸው የነበሩ የተለያዩ የጽ/ቤት እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኛ ሴቶች ብሔራዊ ማኅበር


በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ሲገለገልባቸው የነበሩ የተለያዩ የጽ/ቤት እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች፡-

  1. ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ንብረቱ በሚገኝበት አድራሻ አዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 4፣ የቤቁ 1057 የኢትዮጵያ የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ ፓርክ መግቢያ ፊት ለፊት ወደ ችሎት አደባባይ በሚገነጠለው አስፋልት 7ዐ ሜትር ያህል ገባ ብሎ በሚገኘው ጽ/ቤታችን ከጠዋቱ 3፡ዐዐ እስከ ቀኑ 10፡ዐዐ ሠዓት ድረስ በአካል ቀርበው ማመልከት ይቻላል።
  2. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ጠቅላላ ዋጋ 2ዐ በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) አሰርተው ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ ከሆነ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በዳሽን ባንክ ወይም በአዋሽ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል።
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ከ5 የሥራ ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
  4. ተጫራቾች የሚሸጡትን ንብረቶች መረጃ የያዘው ሠነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ (Column) ስር የሚገዙበትን ዋጋ በአሀዝ እና በፊደል ያለስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቨሎፕ/ፖስታ በፌዴሬሽናችን ጽ/ቤት በመቅረብ በአስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ነገርግን የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጐኑ በተጫራቹ መፈረም አለበት።
  5. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሠነድ መግዛት ይችላሉ።
  6. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ሙሉ ገንዘቡን ለድርጅቱ ገቢ በማድረግ ንብረቱን የመረከብ ግዴታ አለባቸው። ይህ ካልሆነ በሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ያስያዙት ጨረታ ማስከበሪያ ለድርጅቱ ገቢ ተደርጐ ሁለተኛው አሸናፊ ራሱ ባሸነፈበት ዋጋ ከፍሎ እንዲገዛ ይደረጋል።
  7. ተጫራቾች የድርጅቱ ገንዘብ ያዥ ጋር በመቅረብ የንብረቶቹን ሙሉ መረጃ የያዘ ሠነድ በመግዛት ተጫራቾች የጨረታውን መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ የማይመለስ ብር 200.00 እየከፈሉ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 የሥራ ቀናቶች ውስጥ መግዛት ይችላሉ።
  8. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ ከ5ኛ ቀን እስከ 7ኛው ቀን ደግሞ ንብረቶቹ በአካል የሚታዩበት ሲሆን በ7ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 10፡00 ሠዓት ጨረታው ተዘግቶ በዚያው ቀን ከቀኑ 10፡30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
  9. ተጫራቾች ስለአሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታ ሠነዱ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  10. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 011-1553003/0921-324330/0908569070

የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን (ኢ.አ.ጉ.ማ.ፌ.)

✨ messages.ai_summary
The Ethiopian Federation of Associations of Persons with Disabilities is selling various used office items in their current condition via open bid. Bidders must submit a 20% bid security via CPO or cash. Bid documents cost 200 birr. The federation reserves the right to cancel the tender in whole or in part.
Save Tender