የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በሎት የተገለጹ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ለ3ኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ፡- 05/2017
የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በሎት የተገለጹ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ፣
በዚሁ መሠረት ፡-
- በየዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የገበሩ፤
- የቫት /VAT/ ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ያላቸው፤
- የግብር ከፋይ /TIN/ መለያ ቁጥር ያላቸው፤
- የዕቃና የአገልግሎት አቅራቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶች፤
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1 - 4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ኦሪጅናልና ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ለእያንዳንዱ ሎት ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በሲዳማ ክልል ገቢዎች ባለስልጣን በተከፈተው አካውንት ቁጥር 1000347602028 በማስገባት እስልፒ ይዞ ሲዳማ ከልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢሮ ቁጥር 208 በመቅረብ ሠነዱን መውሰድ ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ማስከበሪያ በ CPO / Bid Bond የ90 ቀን/ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 10,000 በጠቅላይ ፍርድ ቤት ስም በማሰራት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የፋይናንሻል ዶክመንት ኦሪጂናል 1 እና 2 ኮፒ በተለያየ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለጨረታ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም ቴክኒካል ዶክመንት ኦሪጂናል 1 እና ኮፒ 1 በተለያየ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ተከታታይ ቀናት ቅዳሜና እሁድ ጨምሮ ከ15 ቀን በኋላ በ16ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት ተዘግቶ 8፡45 ሰዓት ላይ ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል/ የስራ ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ዕቃውን በራሱ ወጪ አጓጉዞ መጋዝን ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ በጨረታ መመሪያ መሠረት የጨረታ አሸናፊነቱ በማስታወቂያ ይገለጻል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 046-2-12-55-84/ 09-39-12-60-96
የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት
