የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ነቀምት መንገድ ጥገና ዲስትሪከት የተለያዩ ለሰራተኞች ጥቅም የሚውሉ (አልባሳት፣ ጫማ እና የመፀዳጃ ወረቀት) በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ብቁ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ነቀምት መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ቲ-01/2017
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ነቀምት መንገድ ጥገና ዲስትሪከት የተለያዩ ለሰራተኞች ጥቅም የሚውሉ (አልባሳት፣ ጫማ እና የመፀዳጃ ወረቀት) በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ብቁ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ድርጅቶች በኢትዮጵያ ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በመንግስት የዕቃና አገልግሎት አቅራቢነት በኤጀንሲው ድረ ገፅ (website) የተመዘገቡ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው::
- በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል የዘመኑ ግብር የከፈሉበት ከሚፈለገው ግዥ የተዛመደ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፊኬት እና በጨረታው ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢዎች ቢሮ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ በማቅረብ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰንጋ ተራ ቅርንጫፍ የሒሳብ ቁጥር 1000002579859 በጥሬ ገንዘብ ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ሜክሲኮ ከሚገኘው የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና መ/ቤት (አዲስ አበባ) በመቅረብ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚሆነው በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው፡፡ የጨረታው ሰነድ የተዘጋጀው በአማርኛ ቋንቋ ነው።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ጨረታ ብር 40,000.00 (አርባ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጪ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን አዲስ አበባ ዋና መ/ቤት ግዥ፣ ቡድን ገቢ የሚያደርጉበት የመጨረሻ ቀን ጥር 07 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥር 07 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 አዲስ አበባ ዋና መ/ቤት በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡
ስልክ ቁጥር ፡- 09-10-28-06-09/057-661-20-74/057-661-11-65
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ነቀምት መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
