የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕ/ሐረርጌ ዞን የጨርጨር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ 2017 በጀት አመት ለየተለያዩ ት/ክፍሎች የሚውሉ ቋሚና አላቂ የቴክኒክና ሙያ የስልጠና እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕ/ሐረርጌ ዞን የጨርጨር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 001/2017
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕ/ሐረርጌ ዞን የጨርጨር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ 2017 በጀት አመት ለየተለያዩ ት/ክፍሎች የሚውሉ ቋሚና አላቂ የቴክኒክና ሙያ የስልጠና እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተለዉን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- እቃውን በጥራት ለማቅራብ የሚያስችል ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢዎች ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅርብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች በአቅራቢዎች/በመስኩ ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ መሆን አለባቸው::
- አቅራቢዎች ከአስመጪው ድርጅት ሰርተፍኬት (ጋራንቲ) ማቅረብ አለባቸው ::
- የጨረታ ማስከበሪያ 20,000 (ሃያ ሺህ) ብር በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው ::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) በመክፈል ከላይ በተገለጸው የጽ/ቤቱ አድራሻ (ጭሮ ወይም አሰበ ተፈሪ ከተማ በኮሌጁ ፋይናንስ ቢሮ) በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይቻላል ::
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት እስከ 6/5/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ለተጫራቾች ክፍት ይሆናል ::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የሚጫረቱበትን መወዳደሪያ የአንዱን ዋጋ በመጥቀስ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ውስጥ አድርጎ እስከ 6/5/2017 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ድረስ በጭሮ ከተማ በኮሌጁ ፋይናንስ ቢሮ ገቢ ማድረግ አለባቸው:: ጨረታው በዚሁ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው የጨረታ ተወዳዳሪ ማሸነፉ ከተገለጸበት በኋላ በአስር (10) ቀናቶች ውስጥ ከግዢው ጠቅላላ ዋጋ ላይ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት፡፡
- ለጨረታ ከቀረቡ ዕቃዎች ዝርዝር ዉስጥ ኮሌጁ እስከ 20% ለመጨመር ወይም ለመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
- ተወዳዳሪዎች በጨረታው ሰነድ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ማህተምና ፊርማቸውን ማኖር አለባቸው ::
- ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻችን ፡- በም/ሐሪ ዞን ጨርጨር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ጭሮ አሰበ ተፈሪ
0255511349/0944141498
ጨርጨር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ጭሮ አሰበ ተፈሪ
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕ/ ሐረርጌ ዞን የጨርጨር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
