የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት የሚከተሉት እቃዎችና አገልግሎቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002/2017
የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት የሚከተሉት እቃዎችና አገልግሎቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያዎች 5,000.00 ሎት 2. ደንብ ልብስ 3,000.00
ሎት 3. የጽዳት ዕቃዎች 15,000.00 ሎት 4. የኤሌትሪክ እቃ ግዥ
ሎት 5. የመኪና ኪራይ 3,000.00 ሎች 6. የድንኳን ግዥ 2,000,000
ሎት 7. የመስተንግዶ ግዥ 3,000.00 ሎት 8. ዲኮር 2,500.00
ሎት 9. የመኪና ሰርቪስ 10,000.00 ሎት 10. የሆቴል መስተንግዶ 3,500.00
በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋበዛሉ፡፡
- በዘርፋ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም በፋይናንስ ቢሮ የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ቤተል ፖስታ ቤት አካባቢ በሚገኘው ወረዳ 06 ፋይናንስና ጽ/ቤት 1ኛ ፎቅ ባለው ቢሮ በመገኘት የማይመለስ ብር 250 (ሁለት መቶ ሀምሳ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል፡፡
- ከሎት 1 - ሎት 10 ላሉት ዕቃዎች ላቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ ከ0.5 ያላነሰ ከ2% ያልበለጠ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በመስሪያ ቤታችን የጨረታ ማስከበሪያ ሎቶቹ ፊት ባለው ዋጋ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ስም በማዘጋጀት ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለአንድ እቃ አንድ ዋጋ ብቻ ማቅረብ አለባቸው፤
- ተጫራቾች የተጠቀሱትን እቃዎች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ፤
- የጨረታ ሰነዱን ማቅረቢያ የመጨረሻው ቀን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ሆኖ በ11ኛው ቀን 3፡30 ይታሸጋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በአስራ አንደኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳ 06 ፋይናንስና ጽ/ ቤት ቢሮ ይሆናል፡፡ ሆኖም አስራ አንደኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፤
- አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፤
- ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን እቃዎች ናሙና በሙሉ በየሎቱ ከጨረታው ጋር ማስገባት አለባቸው
- ተጫራቾች የወሰዱትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን መቀየር አይችሉም፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፣ ስልክ ቁጥር 0113696750/0113697524
የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
