የሚዛን ግብርና ኮሌጅ በ2017 በጀት ዓመት ለመማር ማስተማርና ለተለያዩ ሥራዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዕቃዎች በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Mizan Agricultural TVET College (የሚዛን ግብርና ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኮሌጅ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02/2017
የሚዛን ግብርና ኮሌጅ በ2017 በጀት ዓመት ለመማር ማስተማርና ለተለያዩ ሥራዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዕቃዎች በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት፡-
- የፅዳት ዕቃ
- የሠራተኞች ደንብ ልብስ
- የህንጻ መሣሪያዎች
- የምግብ ቤት ዕቃዎች
- ፕላንትና ማሽነሪዎች
- ህንጻና ተገጣጣሚ ዕቃዎች
- የስፖርት አልባሳት እና የውጭ ዝርያ የወተት ጊደሮች
በመሆኑም ጨረታውን ለመጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መስፈርቶች መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ህጋዊ የሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የዘመኑ ግብር የከፈሉና ህጋዊ የአቅራቢነት ፍቃድ ያላቸው
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት እና የግዥ ኤጀንሲ ድረ ገጽ ላይ ተመዝጋቢ የሆኑ
- በመንግሥት ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ያላቸው
- ለሚወዳደሩበት የጨረታ ማስከበሪያ CPO ብር 50,000 /ሃምሳ ሺ ብር/ በተቋሙ ስም የሚያስይዙ
ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በመያዝ ይህ የጨረታ ሰነድ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ሚዛን ተፈሪ በሚገኘዉ የኮሌጁ ግዥ ስራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ የማይመለስ ብር 300 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ሀጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰነዱ በተሸጠበት ሚዛን ግ/ቴ/ሙ/ስ/ኮሌጅ የግዥ ሥራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል። መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0471353136 ወይም 0473350723 ደውለው ይጠይቁ፡፡
የሚዛን ግብርና ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኮሌጅ
