የጂ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ በ2017 ዓ.ም 1ኛ ዙር የስልጠና አገልግሎት የሚውሉ የእስቴሽነሪ፣ የአይሲቲ፣ የግብርና ፈርኒቸር ፤የሰርቬይንግ፣ የኮንስትራከሽን፣ የአውቶሞቲቭ ፣የኤሌክትሮ ቴክኖሎጂ እና የጋርመንት፣ የስልጠና መሳሪያዎች በሃገር አቀፍ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Jinka Polytechnic College (የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ)
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጂ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ በ2017 ዓ.ም 1ኛ ዙር የስልጠና አገልግሎት የሚውሉ የእስቴሽነሪ፣ የአይሲቲ፣ የግብርና ፈርኒቸር ፤የሰርቬይንግ፣ የኮንስትራከሽን፣ የአውቶሞቲቭ ፣የኤሌክትሮ ቴክኖሎጂ እና የጋርመንት፣ የስልጠና መሳሪያዎች በሃገር አቀፍ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ላይ ለመወዳደር/ለመሳተፍ የምትፈልጉ አቅራቢዎች፤
በዚሁ መሠረት -
- አግባብነት ያለው የዘመኑ ንግድ ፈቃድ ያለው፣
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለውና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ የዘመኑን የግብር ግዴታውን የተወጣ በጨረታ ለመሣተፍ የሚችሉበት ከሚመለከተው አካል ለ2017 ዓ.ም ንግድ ፈቃድ፣ ማስረጃ እና በፋ/ኢ/ል/ቢሮ በአቅራቢነት የተመዘገቡበት ደብዳቤ ፎቶ ኮፒ በመያዝና የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በጂ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ የባንከ አካውንት ቁጥር 1000040809299 ላይ ገቢ በማድረግ የባንክ እስሊፕ በመያዝ በጂ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 203 መጥተው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር የጨረታ ማስከበሪያ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 5000 (አምስት ሺህ ብር) በህጋዊ ባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ አልያም በጥሬ ገንዘብ በማዘጋጀት የጨረታ ሰነድ አንደ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ ፖስታዎችን ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በተገለፁት በአንዱ ወይም በሁሉም መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የመጓጓዣ ወጪ በተጫራቾች የሚሽፈን ሲሆን እስከ ጂ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ ንብረት ክፍል ዕቃውን ገቢ ማድረግ የሚችል ፣
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ዝርዝር ሰነድ ላይ ስምና አድራሻቸውን በግልጽ በመሙላት በማህተምና ፊርማ ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፣
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ16ተኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ያበቃና የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 203 በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው በሥራ ቀን ካልዋለ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይሆናል፤
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር ፦ 0467750459 መጠየቅ ይችላል፡፡
የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
