Tender Detail

Tender Details

  • Company የጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address አሶሳ ፡ ቤኒሻንጉልጉሙዝ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 057-44-83-714
  • Website
  • Deadline01 Jan 2025, 10:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Electrical And Electromechanical

የኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በጉምሩከ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 61 እና 62 በተሰጠው ሥልጣን መሰረት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ከዚህ በታች በተገለፀው የጨረታ መስፈርት መሰረት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


 

ለሁለተኛ ዙር የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር (005/2017)

 

የኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በጉምሩከ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 61 እና 62 በተሰጠው ሥልጣን መሰረት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ከዚህ በታች በተገለፀው የጨረታ መስፈርት መሰረት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ሰርተፊኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡30-6፡00 እና ከሰዓት በኋላ 7፡30-11፡00 ሰዓት ቅዳሜ ጠዋት 2፡30-6፡00 ድረስ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ በመክፈል በጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ዋስትና (CPO) በጉምሩከ ኮሚሽን አሶሳ ቅ/ጽ/ቤት ስም በባንክ በተረጋገጠ አሠርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች ከ18/3/2017 እስከ 23/4/2017 ከጠዋቱ 4፡30 ድረስ አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመምጣት ዕቃዎቹን ማየት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ጨረታው በ23/4/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚያው ዕለት ከረፋዱ 4፡40 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  5. የጨረታው መክፈቻ ቦታ ጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
  6. የጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን አሸናፊ ላልሆኑት ተጫራቾች ደግሞ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  7. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ ከፍያ ከፈፀሙ በ5 ቀናት ውስጥ ዕቃዎቹን ተረክበው ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ከላይ በተራ ቁጥር 7 እና 8 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ዕቃዎቹን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ዕቃዎቹ በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባሉ፡፡
  10. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለተጨማሪ መረጃ 057-44-83-714 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

 

 

Save Tender

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት በ3 ሎት የተከፈሉ ግዥዎችን ለሁለተኛ ዙር በግልፅ ጨ...

READ MORE
MSF Belgium Ethiopia Mission Tender for Supply of Various Types of Stabilizers (Tender Ref. ET121 &...

READ MORE