በአ/አ/ከተማ አስተዳደር የአሽ/ተሽ/ፈ/ቁ/ባለስልጣን የአቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት ለአገልግሎት የሚውሉ የደንብ ልብስ ፣ ቋሚና አላቂ የቢሮ እቃዎችን ማለትም፤ ሎት 1. የደንብ ልብስ፣ ሎት 2. አላቂና ቋሚ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 3. የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 4. የህትመት እቃዎች፣ ሎት 5. የቆዳ ውጤቶች፣ ሎት 6. የተሽከርካሪ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን የአቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02/2017 ዓ.ም
በአ/አ/ከተማ አስተዳደር የአሽ/ተሽ/ፈ/ቁ/ባለስልጣን የአቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት ለአገልግሎት የሚውሉ የደንብ ልብስ ፣ ቋሚና አላቂ የቢሮ እቃዎችን ማለትም፤ ሎት 1. የደንብ ልብስ፣ ሎት 2. አላቂና ቋሚ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 3. የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 4. የህትመት እቃዎች፣ ሎት 5. የቆዳ ውጤቶች፣ ሎት 6. የተሽከርካሪ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በመስኩ የተሰማሩ፣ ህጋዊ እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የኢፌዴሪ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የተ.እ.ታ ተመዝጋቢዎች ለመሆናቸው ኮፒ ማስረጃ እና TIN No ሰርተፊኬት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 - 10፡00 ሰዓትና ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ ቢሮ ቁጥር 39 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ መሰረት የሚወዳደሩበትን ዋጋ በዋጋ ማቅረቢያ /Financial/ ሰነድ፣ እንዲሁም አስፈላጊ ቴክኒካል ሰነዶችን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በመለየት አሪጂናልና ኮፒውን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 31 በመቅረብ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚጫረቱበትን በሎት 1,000 /አንድ ሺህ/ ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን መ/ቤቱ በሰጣቸው ሰነድ ላይ መሙላት እና በእያንዳንዱ የመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ ፊርማ መፈረም እና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና እንዲቀርብ ለተጠየቀባቸው ዕቃዎች ከጨረታ መክፈቻ ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ውሉን ሲዋዋሉ ያሸነፉበትን የጠቅላላ ዋጋውን 10% በባንከ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር 09 11 39 50 76 / 09 22 45 04 40 ደውሎ መጠየቅ ወይም ቃሊቲ ማሰልጠኛ ግቢ ውስጥ ከሚገኘው ቅ/ጽ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 31 በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይቻላል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽ/ተሽ/ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የአቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት
