አምቦ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል በ2017 በጀት ዓመት ለሆስፒታላችን አገልግሎት የሚውል የህሙማን ምግብ ማዘጋጃ ቤት (Kitchen) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
Ambo University (አምቦ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል)
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
አምቦ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል በ2017 በጀት ዓመት ለሆስፒታላችን አገልግሎት የሚውል የህሙማን ምግብ ማዘጋጃ ቤት (Kitchen) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ፡-
- በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ እና የ TIN የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በላይ የሚያወጣ ከሆነ በተጫራቾች እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡበት ማስረጃ አያይዞ ማቅረብ አለበቸው፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ ከመሙላታቸው በፊት ማድቤቱ (Kitchen) የሚሰራበት ቦታ (site) በአካል ተገኝቶ ማየት አለባቸው፡፡
- ለማድቤቱ (Kitchen) መስሪያ የሚሆን ብሎኬት ሆስፒታሉ የሚያቀርብ ሆኖ ሌላው ወጪ በጠቅላላ በአሸናፊው ድርጅት የሚሸፈን ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት በሪፈራል ሆስፒታል ግዢ ክፍል በመገኘት መግዛት ይችላል፡፡
- የጨረታው ውጤት እንደታወቀ ለተሸናፊዎች የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ሲፒኦ አሰርተው ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ በራሳቸው የዋጋ መሙያ ወይም ሆስፒታሉ ባዘጋጀው የዋጋ መሙያ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በጥንቃቄ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በሌሎች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ የሞሉበትን የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል በሰም በታሸገ (ኤንቨሎፕ) አድርገው ጥር 01/2017 ዓ.ም ጠዋት 2፡30 እስከ 3፡30 ሰዓት ድረስ አምቦ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ግዢ ሥራ ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በዚያው ቀን 3:45 ሰዓት ላይ ተጫራቾች በተገኙበት በግዢ የስራ ክፍል ይከፈታል፡፡
- ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የሚቀርብ ተጫራች ተቀባይነት የለውም፡፡
ሪፈራል ሆስፒታሉ የተሸለ አማጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0112609979 ይጠቀሙ::
አምቦ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል
