Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ሪሶርስ ማኔጅመንት ኮሌጅ
  • Address ከተማ ደብረ ዘይት/ቢሾፍቱ የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ሪሶርስ ማኔጅመንት ኮሌጅ ቀበሌ 14/09 ኢንጂነሪግ ግቢ ቢሮ ቁጥር 10 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251114307393
  • Website
  • Deadline10 Jan 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Educational And Training Equipment And Machinery

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ሪሶርስ ማኔጅመንት ኮሌጅ በ2017 ዓ.ም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች አቅራቢዎች አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች በዝርዝር የተገለፁትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን ማወዳደር ይፈልጋል፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ሪሶርስ ማኔጅመንት ኮሌጅ


 

በድጋሚ የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር የኢት/መ ከ/ዩኒቨ/ሪማ/ኮ/ግ/ጨ/02/17

 

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ሪሶርስ ማኔጅመንት ኮሌጅ በ2017 ዓ.ም

  • በሎት አንድ (አላቂ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች እና አላቂ የፅዳት እቃዎች)
  • በሎት ሁለት (የተለያዩ ኮምፒውተሮች እና ፎቶ ኮፒዎች ጥገናና የመለዋወጫ እቃዎች) በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ በዘርፉ ብቃት እና ፍቃድ ካላቸው አቅራቢዎች አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች በዝርዝር የተገለፁትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን ማወዳደር ይፈልጋል፡፡
  1. ተጫራቾች የዘመኑ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የንግድ ምዝገባ መስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በአቅራቢነት መመዝገባቸው የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (vat) ተመዘጋቢ የሆኑ እና ቫት ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ /CPO/ ወይም በባንክ የተረጋገጠ የባንክ ዋስትና ለሎት አንድ 10,000.00 (አስር ሺ ብር) ለሎት ሁለት 10,000.00 (አስር ሺ ብር) በሪሶርስ ማኔጅመንት ኮሌጅ ስም የተሰራ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በየሎቱ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል ከሪሶርስ ማኔጅመንት ኮሌጅ ከግዥ ቢሮ ቁጥር 10 መውሰድ ይችላሉ፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን አሟልቶ ፋይናሺያል ዶክመንት ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ እንዲሁም ቴክኒካል ዶክመንት ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት በግዥ ቢሮ ቁጥር 10 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው አየር ላይ በዋለ በ15ኛው የስራ ቀን ጠዋት 4፡00 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  10. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ናሙና ለተጠየቀባቸው ዕቃዎች የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ከመድረሱ ከአንድ ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር :- +251-11-4-30-73-93 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

አድራሻ ፡- ከተማ ደብረ ዘይት/ቢሾፍቱ የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ሪሶርስ ማኔጅመንት

ኮሌጅ ቀበሌ 14/09 ኢንጂነሪግ ግቢ ቢሮ ቁጥር 10

 

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ሪሶርስ

ማኔጅመንት ኮሌጅ

ቢሾፍቱ

Save Tender