Tender Detail

Tender Details

  • Company Metehara Sugar Factory (መተሐራ ስኳር ፋብሪካ)
  • Address ሜክሲኮ አደባባይ ፊሊፕስ ሕንፃ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115 505607
  • Website
  • Deadline09 Jan 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Health Care, Medical Industry

የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ለ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ለሆስፒታል አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በዝርዝር የተገለፁትን በዘርፍ ከተሰማሩ ሕጋዊ የመድኃኒትና የህክምና መገልገያ አከፋፋዮችን ወይም አስመጪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለሁለት ዓመት የሚቆይ ውል በማሰር ግዥ ማከናወን ይፈልጋል፡፡

Metehara Sugar Factory (መተሐራ ስኳር ፋብሪካ)


የጨረታ  ማስታወቂያ

የጨረታ  ቁጥር  MSF/LP/17/2024

 

የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ለ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ለሆስፒታል አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በዝርዝር የተገለፁትን በዘርፍ ከተሰማሩ ሕጋዊ የመድኃኒትና የህክምና መገልገያ አከፋፋዮችን ወይም አስመጪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለሁለት ዓመት የሚቆይ ውል በማሰር ግዥ ማከናወን ይፈልጋል፡፡

ጥቅል 1 መድኃኒቶች (MEDCINES) በድጋሚ የወጣ ጥቅል 2 የላብራቶሪ ኬሚካሎችና ሪኤጀንቶች (ABORATORY CHEMICALS AND RBEAGENTS) በድጋሚ የወጣ ጥቅል 3: የተለያዩ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች (MEDICAL SUPLLIES) በድጋሚ የወጣ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች እንደሚከተለው ተጋብዛችኋል፡፡

  1. በዘርፉ የተሰማራችሁ የመድኃኒትና የህክምና አከፋፋዮችን ወይም አስመጪዎችን የ2017 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላችሁ እንዲሁም የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈላችሁ፡፡
  2. በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባችሁን ማቅረብ የምትችሉ፡፡
  3. ጉዳዩ ከሚመለከተውና አግባብነት ካለው መንግስታዊ መሥሪያ ቤት የሙያ ፈቃድ ሰርትፊኬት፣ የጥራት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት ፍቃድ፡፡
  4. በጨረታው አሸናፊ የሆኑት ድርጅቶች ላሸነፉበት አይነት በየጊዜው በሚቀርብላቸው የግዢ ትዕዛዝ መሰረት የተለያዩ መድኃኒቶች፣ አላቂ እና ቋሚ የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች የላብራቶሪ ኬሚካሎች እና ሪኤጀንቶች የአቅርቦት አይነት አዲስ አበባ ፊሊፕስ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 215 ግዥ ቡድን ድረስ ማቅረብ የሚችሉ፤
  5. የጨረታ ማስከበሪያ ብር ሃምሳ ሺ (50,000.00) በሲ.ፒ.ኦ /CPO/ ወይም የባንክ ዋስትና /Bid bond guarantee/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. መተሐራ ስኳር ፋብሪካ ግዥ ቡድን አዲስ አበባ ሜክሲኮ አደባባይ ፊሊፕስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 215 ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የንግድ ፈቃድ ይዘው በመቅረብ ለእንዳንዱ ጥቅል የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) እየከፈሉ የጨረታውን ሠነድ በመውሰድ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ (Proforma invoice) ላይ በማዘጋጀት በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ እ.ኢት.አ. ጥር 01 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4:00 ሠዓት ድረስ መተሐራ ስኳር ፋብሪካ ግዥ ቡድን አዲስ አበባ ሜክሲኮ አደባባይ ፊሊፕስ ህንፃ 2ኛ ፎቅቢሮ ቁጥር 215 ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው በዕለቱ ጥር 01 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ላይ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር n9 ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  9. ፋብሪካው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ስልክ ቁጥር  0115-505607/0115-505633

ሜክሲኮ  አደባባይ ፊሊኘስ  ሕንፃ

አዲስ  አበባ

 

የመተሐራ  ስኳር ፋብሪካ

Save Tender