በጋም/ህ/ብ/ክ/መንግስት የክልሉ ትራንስፖርት ቢሮ በ2017 ኣ.ም በጀት ዓመት የመነኻሪያ ግራና ቀኝ በር ግንባታ ማስገንባት በደረጃ G.C-6 እና ከዚያ በላይ ያሉትን የሥራ ተቋራጮች በማወዳደር ማሰራት ይፈልጋል።
የጋምቤላ ህዝብ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትራንስፖርት ቢሮ
የጨረታ ማስታወቂያ
በጋም/ህ/ብ/ክ/መንግስት የክልሉ ትራንስፖርት ቢሮ በ2017 ኣ.ም በጀት ዓመት የመነኻሪያ ግራና ቀኝ በር ግንባታ ማስገንባት በደረጃ G.C-6 እና ከዚያ በላይ ያሉትን የሥራ ተቋራጮች በማወዳደር ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፤
- የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሠርተፍኬት ያለው፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፤
- ከውዝፍ ግብር ነፃ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፤
- የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ያለው፤
- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ተጫራቾች ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሠነድ የማይመለስ 1,500.00 /አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከክልሉ ትራንስፖርት ቢሮ የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ዋስትና ማስከበሪያ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) ብር በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ ብቻ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ግንባታው የሚያከናውኑበትን ዋጋ ዋናውንና ኮፒ አንድ /1/ እና ካምፓኒ ፕሮፋይል ዋናውንና ኮፒ አንድ /1/ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በ22ተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30-4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ አስገብተው በዚሁ ቀን በ4፡50 ሰዓት ላይ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በክልሉ ትራንስፖርት ቢሮ ጊቢ ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0911040858 ይጠቀሙ።
የጋም/ህ/ብ/ክ/መንግስት የትራንስፖርት ቢሮ
