Tender Detail

Tender Details

  • Company በወላይታ ዞን የድጉና ፋንጎ ወረዳ ፋይናንስ /ጽ/ቤት
  • Address ወላይታ ዞን ቢጠና : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-16-71-99-03
  • Website
  • Deadline11 Jan 2025, 4:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Building Construction

በደቡብ ኢትየጵያ ክ/መ/ በወላይታ ዞን የድጉና ፋንጎ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ከወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት እና ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ጋር በመሆን በ2017 በጀት ዓመት በዋን ዋሽ ናሸናል ፕሮግራም በተላከው በጀት በትምህርት ቤት ግብ የሴቶች ንጽህና መጠበቅያ ቤት/ MHM/ ቤት ግንባታ ሥራዎች እና በጤና ኬላዎች ባለ ሁለት ክፍል መጸዳጃ ቤት ግንባታ ሥራዎች በግልጽ ጨረታ ህጋዊ ተወዳዳሪዎችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

በወላይታ ዞን የድጉና ፋንጎ ወረዳ ፋይናንስ /ጽ/ቤት


የጨረታ  ማስታወቂያ

 

በደቡብ ኢትየጵያ ክ/መ/ በወላይታ ዞን የድጉና ፋንጎ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ከወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት እና ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ጋር በመሆን በ2017 በጀት ዓመት በዋን ዋሽ ናሸናል ፕሮግራም በተላከው በጀት በትምህርት ቤት ግብ የሴቶች ንጽህና መጠበቅያ ቤት/ MHM/ ቤት ግንባታ ሥራዎች እና በጤና ኬላዎች ባለ ሁለት ክፍል መጸዳጃ ቤት ግንባታ ሥራዎች በግልጽ ጨረታ ህጋዊ ተወዳዳሪዎችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

ሎት 1 - በትምህርት ጽህፈት ቤት በቢጠና ሐሙስ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እና በድጉና ኦፋ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ /MHM/ ቤት ግንባታ ሥራዎች፤

ሎት 2 - በጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት በፋንጎ ክንዶ ቀበሌ ዞንጋ እና በፋንጎ ሶሬ ቀበሌ ደጋ ጤና ኬላዎች ላይ ባለ ሁለት ከፍል መጸዳጃ ቤት ግንባታ ሥራዎች፤

ሎት 3 - በጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት በኤዶ ቦሎሶ ጤና ኬላ ላይ ባለ ሁለት ክፍል መጸዳጃ ቤት ግንባታ እና በቢላቴ ጫርቾ ቀበሌ ጤና ኬላ ላይ 10,000 ሌትር ሮቶ ከነማስቀመጫ ግንባታ ሥራዎች፤

በዚህ መሠረት መጫረት የምትችሉ ተጫራቾች  -

  1. የ2017 ዓ.ም ፈቃዳቸው ያሳደሱ የታደሰ ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤ ቲ.ኦ.ቲ/ ቫት ተመዝጋብ የሆኑ፤ የቲን መለያ ቁጥር ያላቸው፤ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸውና በፌዴራል ግዥና የመንግስት ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ምዝገባ በበይነ መረብ የተመዘገቡበትን ማቅረብ የሚችሉ እና ደረጃ BC/GC-6 እና ከዛ በላይ ያላቸው፡፡
  2. 2% ለመንግስት ግብር እንደሚቆረጥ ማወቅ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ) ብር በመከፈል ከወ/ድ/ ፋ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የንግድ ፍቃዳቸውን ዋናውን በመያዝ ከቢሮ ቁጥር 13 መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸውን ቴክኒካል ግምገማ መስፈርቱን ከዋናው ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፤ (የጨረታው ሰነድ ከጨረታ ማስታወቂያ ጋር እኩል ዋጋ ይኖረዋል)።
  5. ተጫራቾች በአሁኑ ሰዓት ያላጠናቀቁና በውል ያላስረከቡ ፕሮጀክት በእጃቸው ካለ ጨረታውን ለመወዳደር ብቁ አይደሉም ወይም ከጨረታው ውድቅ ይሆናሉ። (ተጫራቾች ፕሮጀክቱን ያጠናቀቁበትን የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማቅረብ ይኖርባቸዋል)።
  6. እያንዳንዱ ዶክመንት በተጫራቾች መመሪያ መሰረት ተሞልተው/ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ ሁሉንም ለየብቻቸው ታሽገው እና የጨረታ ማስከበሪያውን በተለየ ፖስታ ለብቻው በማቅረብ ሁሉም ዶክመንት በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ በሰም አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳዱ ሎት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ካሽ ብር 15,000 (አስር አምስት ሺህ ብር) ጨረታው ከተከፈተ ለ60 ቀናት የሚቆይ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  8. ተጫራቾች የመስክ ምልከታ ድጋፍ ከወረዳው ጤና ጥበቃ እና ትምህርት ቤቶች ጽ/ቤት መቀበል ይኖርባቸዋል።
  9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ላይ የማይናበብና ስርዝ ድልዝ ያለው መሆን የለበትም፡፡
  11. ስለዚህ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ በ21 /ሃያ አንድ/ ተከታተይ የሥራ ቀናት ከቀኑ 10፡00 AM ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን የሚቆይ ሲሆን 21ኛው ቀን በዓል እና ሰንበት ከሆነ ቀጣይ በሥራ ቀን 10፡00 AM ከላይ የተገለፀውን መሥፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን ዋጋ በመግለጽ ፖስታውን በሰም አሽገው ዘወትር በሥራ ሰዓት ድ/ፋ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስተዳደር ዋና የሥራ ሂደት ጨረታ ክፍል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማኖር ይችላሉ።
  12. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም፣ ባልተገኘበትም ልክ ቀኑ 10፡30 AM ሲሆን የፖስታ ሳጥን በ10:00 AM ከሰዓት ታሽጎ በ10:30 A.M ሰዓት ይከፈታል።
  13. የሃሳብ ማስተካከያ ስህተት ከ2% በላይና በታች መሆን የለበትም።

ለበለጠ  መረጃ  ስልክ  ቁጥር ፡- 09-16-71-99-03/ 09-66-52-35-51/ 09-16-11-42-41

 

የወላይታ ዞን የድጉና ፋንጎ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender