የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳ 13 አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የመስተንግዶ ህትመት እና ድንኳን ኪራይ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳ 13 አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የመስተንግዶ ህትመት እና ድንኳን ኪራይ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉና በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታከስ ከፋይነት (VAT) የተመዘገቡበት የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ፋይናንስ ጽ/ቤት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ በCPO ማስያዝ የሚችሉ።
- የመወዳደሪያ ዋጋውን ከነቫት በማስቀመጥ በግልጽ ተጠቅሶ መፃፍ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታው ተሳታፊዎች የሚያቀርቡበትን የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ያሸነፋ ተጫራቾች ደረጃቸውን የጠበቁ ዕቃዎችን ትዕዛዙ በደረሳቸው ጊዜ ወዲያውኑ በተፈለገው ቦታ ወይም እስቶር ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3:30 የጨረታው ሣጥን ይታሸጋል፡፡ በዚያው እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ወረዳ 13 ፋይናንስ ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታው ሳጥን ይከፈታል፡፡
- ወረዳው የሚፈልጋቸው ደረጃቸውን የጠበቁ የመስተንግዶ ህትመት እና የድንኳን ኪራይ ዋጋ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የሚያስፈልጋቸው የቆሎና የውሃ ናሙና በአካል ሌሎቹን በፎቶ እንድታቀርቡ እናሳውቃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር 0116678556 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻ ፡- የተባበሩት አደባባይ ከፀሐይ ሪል እስቴት ወደ አይሲኤምሲ ሆስፒታል መሄጃ መንገድ ላይ 500 ሜትር ገባ ብሎ ወይም ከአፍሪካ ኮንፌንሽን ጀርባ ይገኛል፡፡
የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ፋይናንስ ጽ/ቤት
