የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት
በድጋሚ ለ2ኛ ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
|
ተ.ቁ |
ጨረታ የሚወጣ የእቃው ዓይነት |
ሎት |
|
1 |
የደንብ ልብስ |
1 |
|
2 |
የስቴሽነሪ ዕቃዎች |
2 |
|
3 |
የፅዳት ዕቃዎች |
3 |
|
4 |
አላቂ የቢሮ ዕቃዎች |
4 |
|
5 |
የህትመት ውጤቶች |
5 |
|
6 |
ቋሚ ዕቃ |
6 |
|
7 |
የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጥገና/ፕሪንተር፣ኮምፒውተር፣ ላፕቶፕ፣ ፎቶ ኮፒ ማሽን፣ ጀነሬተር የኔትዎርክ ዝርጋታ ከነዕቃውና የእጅ ዋጋን ጨምሮ |
7 |
|
8 |
ትራንስፖርት የሚያቀርብ /አውቶብስ ፣ ወይም ሀይገር፤ የሕዝብ ማመላለሻ መኪና፣⁄ አይሱዙ የጭነት መኪና |
8 |
|
9 |
መስተንግዶ/ ቆሎ፣ ውሃ 1/2፣ ኩኪስ፣ ድፎ፣ ዳቦ፣ የጠርሙስ ለስላሳ |
9 |
|
10 |
የአትክልት ዘር |
10 |
በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሕጋዊ ሰነዶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች መሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- የዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) በየሎቱ ብር 10,000.00 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉበት ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ቦታው ድረስ ማቅረብ (ማስገባት) ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሽገ ፖስታ ውስጥ በመሙላት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡(ሲፒኦ ኮፒ ውስጥ ይግባ)
- ተጫራቾች የአንዱን ዋጋ ቫትን ጨምሮ ወይም ቫትን ያካተተ ተደርጎ ይሞላ፡፡
- ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነድ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሰነዱ የመግዣ ዋጋ የማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ /ብር ብቻ በመክፈል በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ላይ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የሞሉትን ዋጋ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ7 የሥራ ቀናት በኋላ ውል በመግባት በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዕቃውን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ጽ/ቤት ታሽጎ ወዲያው 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳ 05 ፋይናንስ ጽ/ቤት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ሆኖም ጨረታው የሚከፈትበት የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- መሥሪያ ቤታችን የተሻለ፤ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-0114165909/ 014703280 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
- አድራሻ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ቄራ ቀስተ ዳመና ስፖንጅ ፋብሪካ ኖክ ማደያ አጠገብ፡፡
- በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተወዳዳሪዎች ከሆኑ አምራች ለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው።
- ለሚያቀርቡት እቃዎች በሙሉ ተወዳዳሪ ነጋዴዎች የጥራት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት
