የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አቃቂ በሚገኘው መጋዘን ውስጥ ያገለገሉ ልዩ ልዩ ብረታ ብረቶች፣ ፕላስቲኮች እና ማሽነሪዎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
Ministry of Innovation and Technology (የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር)
ያገለገሉ ልዩ ልዩ ብረታ ብረቶች ፤ ፕላስቲኮች እና ማሽነሪዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2017
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አቃቂ በሚገኘው መጋዘን ውስጥ ያገለገሉ ልዩ ልዩ ብረታ ብረቶች፣ ፕላስቲኮች እና ማሽነሪዎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው እና ልዩ ልዩ ብረታ ብረቶች፣ ፕላስቲኮች፣ ጊዜያዊ ክምችት፣ የመነቃቀልና ድጋሚ የመጠቀም እንዲሁም የተለያዩ ክፍልፋዮችን የማስወገድ ፍቃድ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የተሰጠውና የቴክኒክ ብቃት ያለው፣ ለዚህ አገልግሎት የሚውል የተሟላ ወርክ ሾፕ ያለውና በአካል ማሳየት የሚችል እንዲሁም ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃና መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- በኢኖቬሽንና ቴከኖሎጂ ሚኒስቴር ግቢ ውስጥ ግዥ አገልግሎት ቢሮ በመምጣት የንብረቶችን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ 200 ብር /ሁለት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000263705916 ከፍለው ደረሰኝ በማምጣት መውሰድ ይችላሉ፤
- ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ልዩ ልዩ ንብረቶችን ከላይ በተጠቀሰው መ/ቤት በመሄድ መመልከት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች የሚገዙትን ልዩ ልዩ ንብረቶች የጨረታ መነሻ ዋጋ 10 በመቶ ማስከበሪያ በሚ/ር መስሪያ ቤቱ ስም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ኢኖቬሽንና ቴከኖሎጂ ሚ/ር 3ኛ ፎቅ መሰረታዊ አገልግሎት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
- የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢኖቬሽንና ቴከኖሎጂ ሚ/ር 3ኛ ፎቅ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመከፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ፈቃድ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፤
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ7 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፤
- የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ነው፡፡ የሚወዳደሩባቸውን ልዩ ልዩ ንብረቶች የመነሻ ዋጋ 10 በመቶ ያላስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፤
- የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፤
- አገልግሎቱ ባወጣው ጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፤
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረቶቹን በ10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፣
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0913-232728/ 0911-907148/ 0973513788/ 0986-346652 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፤
- መ/ቤቱ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የማያስችል ሁኔታ ከተፈጠረ በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
