የሆሣዕና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ በ2017 ዓ/ም ለኮሌጁ ሥራ አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሎት 2 የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች እና የፋርማሲና ኬሚካል ዕቃዎች፣ ሎት 3 የጽሕፈት መሣሪያዎች ፣ ሎት 4 የኤሌክትሪክና የጥገና ዕቃዎች ፣ ሎት 5 የደንብ ልብስ ፣ ፍራሽና የፍራሽ ጨርቅ፣ የተማሪዎች ጋዎን እና የመመረቂያ ጋዎን ፣ ሪቫን እና ቆብ ፣ ሎት 6 የጽዳት ዕቃዎች እና ሎት 7 ፈርኒቸር ዕቃዎች።
የሆሣዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
የጨረታ ማስታወቂያ
የሆሣዕና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ በ2017 ዓ/ም ለኮሌጁ ሥራ አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሎት 2 የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች እና የፋርማሲና ኬሚካል ዕቃዎች፣ ሎት 3 የጽሕፈት መሣሪያዎች ፣ ሎት 4 የኤሌክትሪክና የጥገና ዕቃዎች ፣ ሎት 5 የደንብ ልብስ ፣ ፍራሽና የፍራሽ ጨርቅ፣ የተማሪዎች ጋዎን እና የመመረቂያ ጋዎን ፣ ሪቫን እና ቆብ ፣ ሎት 6 የጽዳት ዕቃዎች እና ሎት 7 ፈርኒቸር ዕቃዎች።
- በየዘርፋ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የአቅራቢነት የምዝገባ ምስከር ወረቀት፣ የታክስ ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት (TIN) አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ ማስረጃ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንከ (CPO) በጨረታ የተወዳደሩበት ዕቃ በአይነት ብር 5000 / አምስት ሺህ ብር/ ብቻ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይኖርባቸዋል ፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ የሚያቀርቡት ኮሌጁ ለጨረታ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ብቻ ሲሆን ኮሌጁ ካዘጋጀው ሰነድ ውጪ የሚቀርቡ የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
- ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን ዕቃዎች የሚያቀርቡበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻው ማቅረብ አለባቸው ፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል መንግሥት በሆሣዕና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ግዥ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 10 የማይመለስ ብር 200 / ሁለት መቶ ብር / ብቻ በሆሣዕና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሣብ ቁጥር 1000021172867 ላይ ገቢ በማድረግ ደረሰኝ አቅርቦ ጨረታ መግዛት የሚቻል ሲሆን በመጨረሻው 15ኛ ቀን 11፡30 ሰዓት የጨረታ ሠነዱ ሽያጭ ያበቃና የጨረታ ሰነድ ዋናውና ኮፒ ለየብቻው በተለያዩ ፖስታዎች ታሽጎ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ በተካሄደበት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በሆሣዕና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ግዥና ንብረት አስተዳደር 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 10 ለአገልግሎት በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት የሚቻል ሆኖ የጨረታ ሠነድ ማስገቢያ ሣጥን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይታሸግና በ16ኛው ቀን በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ሽያጩ በተካሄደበት ቦታ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሰዓቱ በቦታው ያለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም ፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በሆሣዕና ጤና ሣይንስ ኮሌጁ ግዥና ንብረት አስተዳደር 3ኛ ፎቅ ቢር ቁጥር 10 ይከፈታል ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለ90 ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የሚሠጡት የጨረታ ዋጋ ለ3 ወር ፀንቶ የሚቆይ መሆን መቻል አለበት፡፡
- ኮሌጁ ዕቃውን ርክክብ የሚፈጽመው ኮሌጅ ግቢ ንብረት ክፍል ውስጥ ነው ::
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ
በስልክ ቁጥር - 09-13-56-82-48 ፤ 09-13-22-65-52 እና 09-13-10-08-89 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሆሣዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
