ወማ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገ/ግ/ስራ ዩኒየን ለ2017/18 የምርት ዘመን የሚውል NPSB Nps እና UREA የአፈር ማዳበሪያ በቀቤና ልዩ ወረዳ ለማሰራጨት ህጋዊ የሆነ ሀገር ውስጥ ደረቅ ጭነት ትራንስፖርት ድርጅቶችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
የወማ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገ/ህ/ስራ ዩኒየን
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ወማ 10001/2017 ዓ.ም
ወማ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገ/ግ/ስራ ዩኒየን ለ2017/18 የምርት ዘመን የሚውል NPSB Nps እና UREA የአፈር ማዳበሪያ በቀቤና ልዩ ወረዳ ለማሰራጨት ህጋዊ የሆነ ሀገር ውስጥ ደረቅ ጭነት ትራንስፖርት ድርጅቶችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርቶች ማሟላት የሚችል በዘርፉ የተሰማራ ማንኛውም የሀገር ውስጥ የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት ባለንብረት በጫረታው መሳተፍ የሚችል መሆኑን እንገልፃለን ፡፡
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ፡-
- በደረቅ ጭነት ትራንስፖርት ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማረጋገጫ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው ፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከወማ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዩኒየን ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ ዘወትር በስራ ሰአት መውሰድ ይችላል ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና 100,000 /አንድ መቶ ሺ ብር/ ሲፒኦ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል ።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከዩኒየኑ ሂሳብ ከፍል የጨረታ ሰነድ መግዛት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በ10ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ላይ ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 በዩኒየኑ ጽ/ቤት ይከፈታል።
- ማንኛውም ተጫራች በግዴታ ውስጥ የተካተቱትን ህጎች ማክበር የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ዩኒየኑ በትራንስፖርት በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
- ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 0911993344/0913339674/0912242711
የወማ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገ/ህ/ ስራ ዩኒየን
