በአዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ የመንገድ ግንባታ ማሽነሪዎች (ASPHALT PAVER MACHINE: CRAWLER CRANE MACHINE CEMENT SILO MACHINE) በሀራጅ ጨረታ እንዲሁም የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፣ የሞባይል ከፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የተያዙና የተወረሱ የመንገድ ግንባታ ማሽነሪዎች
እና ልዩ ልዩ ዕቃ ሽያጭ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 21/2017
በአዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ የመንገድ ግንባታ ማሽነሪዎች (ASPHALT PAVER MACHINE: CRAWLER CRANE MACHINE CEMENT SILO MACHINE) በሀራጅ ጨረታ እንዲሁም የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃ ተዘጋጅቶ ከሀሙስ ታህሳስ 10/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑን እንገልጻለን።
በመሆኑም:-
- በመንገድ ግንባታ ማሽነሪዎች ሀራጅ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች የመንገድ ግንባታ፣ የኮንስትራክሽን፣ የማሽነሪ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ሊሆኑ ይገባል፡፡ በተጨማሪም በተ.ቁ 2 የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይገባቸዋል፡፡
- በግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (CPO) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- በጨረታው ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም።
- ተጫራቾች የመንገድ ግንባታ ማሽነሪዎች እና የዕቃዎቹን ጨረታ ሰነድ ከሀሙስ ታህሳስ 10/2017 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ በመገኘት የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- በዕቃ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) በቅ/ፅ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የመንገድ ግንባታ ማሽነሪዎች ሀራጅ ጨረታ ለመሳተፍ ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ማሽሪዎች ብር 100,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) በተ.ቁ 5 በተገለጸው አድራሻ ተጫራቹ የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) ማስያዝ አለበት፡፡
- ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ፡፡
|
ተ.ቁ |
የቅ/ጽ/ቤቱ ስም |
የጨረታው አይነት |
የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነድ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ |
የጨረታው የመዝጊያ እና የመከፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ፅ] ቤት
|
የእቃ ግልፅ
|
እስከ 15/04/2017 |
16/04/2017 3:45 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 4፡00 ሠዓት ይከፈታል |
|
የመንገድ ግንባታ ማሽነሪዎች ሀራጅ ጨረታ |
እስከ 16/04/2017 |
17/04/2017 4፡00 ሠዓት ጀምሮ ይካሄዳል። |
- የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡
- ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል፡፡
- ከላይ በተ/ቁ 10 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ከፍያዉን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃዉ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡- አዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ ፡- 011-470-85-03
አድራሻ ፡- ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው መንገድ ኖክ ማደያ ያለበት አዲሱ ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ
አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
