Tender Detail

Tender Details

  • Company National Alcohol and Liquor Factory (ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ)
  • Address መካኒሳ ዋናው መስሪያ ቤት ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0711460279
  • Websitehttps://www.nalf.com.et/
  • Deadline26 Dec 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Transportation Service And Cargo

ድርጅታችን ከመከኒሳ ዋናው መስሪያ ቤት ፋብሪካ እና ከሰበታ ቅ/ፋብሪካ ተረፈ ምርት /ቆሻሻ/ በመጫን አጓጉዞ የሚወገድበት ቦታ በእራሱ አመቻችቶ የሚያራግፍ ተሽከርካሪ በጨረታ አወዳድሮ ውል በመፈራረም ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

National Alcohol and Liquor Factory (ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ)


የጨረታ  ማስታወቂያ  የጨረታ  ቁጥር

036/2017 ዓ.ም

 

ድርጅታችን ከመከኒሳ ዋናው መስሪያ ቤት ፋብሪካ እና ከሰበታ ቅ/ፋብሪካ ተረፈ ምርት /ቆሻሻ/ በመጫን አጓጉዞ የሚወገድበት ቦታ በእራሱ አመቻችቶ የሚያራግፍ ተሽከርካሪ በጨረታ አወዳድሮ ውል በመፈራረም ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች

  1. በዘርፉ አገልግሎት የመስጠት የታደሰ ፍቃድና የዘመኑ ግብር ለመክፈላችሁ መረጃ ማቅረብ የምትችሉ፡፡
  2. የመጫን አቅሙ እስከ 20,000 ሊትር ወይም 200 ኩንታል ፈሳሽ ወይም ደረቅ ተረፈ ምርት ቆሻሻ የሚጭን መኪና ማቅረብ የሚችል
  3. የሚያቀርቡት ዋጋ በአንድ ጊዜ ለሚጓጓዘው ተረፈ ምርት ቆሻሻ/ ሲሆን ለሰበታ እና መከኒሳ ፋብሪካዎች ለየብቻ ዋጋ መቀመጥ አለበት፡፡ የሚቀርበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለመሆኑ በግልፅ መቀመጥ አለበት፤
  4. የሚቀርበው ዋጋ የሹፌር ደመወዝ ፣ ነዳጅና ሌሎች አጠቃላይ የተሽከርካሪውን ወጪ ያካተተ መሆን አለበት፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና የሚሆን 10,000 ብር በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የሚያስገቧቸውን ሠነዶች ታህሳስ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት መካኒሳ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት 5ኛ ፎቅ ግዥ ቢሮ ቁጥር 503 ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ጨረታው በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡10 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  7. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ፓ.ሣ.ቁ. ፡- 3516 ስልክ ቁጥር 0113690563 ፋክስ 0113690563

 

የብሔራዊ  አልኮልና  አረቄ  ፋብሪካ

Save Tender