Tender Detail

Tender Details

  • Company ቶኩማ አዳማ አክሲዮን ማህበር
  • Address አዳማ ከተማ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline29 Dec 2024, 5:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing

የቶኩማ አዳማ አከሲዮን ማህበር ህጋዊ የሙያ ፈቃድ ያለው ቻርተርድ ሰርቲፋይድ አካውንታንትስ እና የተፈቀደለት የውጪ አዲተር በውጪ አዲተርነት ሙያ ከታወቀ አካል ህጋዊ ሰርተፍኬት እና ሌሎች የሙያ ፈቃድ ያላቸውን ባለሙያዎች አወዳድሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እና ሌሎች በስራ ሂደት የሚከሰቱ ስራዎችን ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

ቶኩማ አዳማ አክሲዮን ማህበር


ለውጪ  ኦዲተሮች  የተዘጋጀ  የስራ

ጨረታ  ማስታወቂያ

 

የቶኩማ አዳማ አከሲዮን ማህበር ህጋዊ የሙያ ፈቃድ ያለው ቻርተርድ ሰርቲፋይድ አካውንታንትስ እና የተፈቀደለት የውጪ አዲተር በውጪ አዲተርነት ሙያ ከታወቀ አካል ህጋዊ ሰርተፍኬት እና ሌሎች የሙያ ፈቃድ ያላቸውን ባለሙያዎች አወዳድሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እና ሌሎች በስራ ሂደት የሚከሰቱ ስራዎችን ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት -

    1. አጠቃላይ የድርጅቱን የፋይናንስ እንቅስቃሴ ከ2008 ዓ.ም እስከ 2017 ዓ.ም ያለውን ልዩ የምርመራ ኦዲት ማስደረግ
    2. የተከናወኑ የግንባታ ስራዎች ላይ ልዩ ምርመራ ማካሄድ
    3. የግንባታ ግብዓቶች እና ሌሎች የትምህርት ግብዓት ግዢ ሲፈጸም እና የጥገና ስራዎችን ሲሰሩ ህጋዊነታቸው ላይ ልዩ የምርመራ ኦዲት ማድረግ
    4. የሚድ ላንድ ኮሙኒቲ ት/ቤት በአክሲዮን ማህበሩ ሲገዛ የነበረውን ግዢ እና የጥቅም ግጭት ማጣራት፣
    5. የሼር ግዢ፣ የድልድል እና ሽያጭ (ማስተላለፍ) ሂደትን መመርመር
    6. የሰራተኛ ቅጥር፣ እድገት፤ የደመወዝ ጭማሪ እና ስንብትን በተመለከተ ህግና ደንብን ተከትሎ መከናወኑን ማረጋገጥ
    7. በምስረታ ላይ የተከፈለ 10% የአገልግሎት ክፍያ በማን አካውንት እና ስም እንዳለ ማረጋገጥ
    8. ከአክሲዮን ማህበሩ እውቅና ውጪ በግለሰቦች ስም የተከፈቱ የባንከ አካውንቶች ላይ ህጋዊነታቸውን ማረጋገጥ
    9. ሀላፊነትን ካለአግባብ መጠቀም እና ስልጣንን አለአግባብ በመጠቀም የደረሰ ኪሳራን ማጣራት
    10. የቋሚና አላቂ ንብረቶች ግዢ ህጋዊነትና ንብረቱ መኖሩን ማረጋገጥ

በመሆኑም ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን የአከሲዮን ማህበሩን ስራዎች ለመስራት ፈቃደኛ እና ህጋዊ የሙያ ፈቃድ ያለው ቻርተርድ ሰርቲፋይድ አካውንታንትስ እና የተፈቀደለት የውጪ ኦዲተር መወዳደር ይችላል፡፡ ስለዚህ የሚሰሩበትን ዋጋ እና አስፈላጊ መረጃዎች በማጠናቀር የዘመኑን ግብር የነበረ እና የታደሰ የሙያ ፈቃድ በማያያዝ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት አዳማ ከተማ በሚገኘው በቶኩማ አዳማ አክሲዮን ማህበር ዋና ጽ/ቤት በታሸገ ፖስታ በማስገባት ማቅረብ ይችላል።

 

ቶኩማ  አዳማ  አክሲዮን  ማህበር

Save Tender