የኢትዮጵያ ኦፕቶሜትሪ ባለሙያዎች ማኅበር በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አዋጅ 1113/2011 በኤጀንሲው ቁጥር 2913 የተመዘገበ የሙያ ማኅበር ሲሆን ከህዳር 01 ቀን 2016 እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ያለውን የማኅበሩን የሂሳብ ሥራ በውጪ ኦዲተር ማስመርመር ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ኦፕቶሜትሪ ባለሙያዎች ማኅበር
በድጋሚ የወጣ የኦዲት ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ኦፕቶሜትሪ ባለሙያዎች ማኅበር በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አዋጅ 1113/2011 በኤጀንሲው ቁጥር 2913 የተመዘገበ የሙያ ማኅበር ሲሆን ከህዳር 01 ቀን 2016 እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ያለውን የማኅበሩን የሂሳብ ሥራ በውጪ ኦዲተር ማስመርመር ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ድርጅቶችን በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
- የሰርቲፋይድ ቻርተርድ አካውንታንት የሆኑና ኦዲት የማድረግ ሕጋዊ የሙያ ፈቃድ እንዳላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ለ2017 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ወይም ጨረታው እስከሚከፈትበት ቀን ድረስ ሊያገለግል የሚችል የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ወቅታዊ ክሊራንስ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት (ግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት) እና 5000 ብር (አምስት ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡ ሆኖ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ቫትን ያካተተ ፋይናንሺያልና ቴክኒካል ፕሮፖዛል በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለማኅበራችን ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከ2፡30-10፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል አራት ኪሎ፣ ቱሪስት ሆቴል ጀርባ ተሰኒም ሕንጻ ሁለተኛ ፎቅ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኦፕቶሜት ባለሙያዎች ማኅበር ቢሮ መግዛት የሚችሉ።
- ተጫራቾች ሥራውን ሠርተው የሚጨርሱበትን ቀን በመጥቀስ ማስገባት የሚችሉ።
- ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0910038040 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻችን ፡- አራት ኪሎ፣ ቱሪስት ሆቴል ጀርባ፣ ተስኒም ሕንጻ ሁለተኛ ፎቅ፤ የኢትዮጵያ ኦፕቶሜትሪ ባለሙያዎች ማኅበር ቢሮ
የኢትዮጵያ ኦፕቶሜትሪ ባለሙያዎች ማኅበር
