Tender Detail

Tender Details

  • Company Ambo University (የአምቦ ዩኒቨርሲቲ)
  • Address አምቦ ፡ ኦሮሚያ ክልል፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-2-363825
  • Websitehttps://ambou.edu.et/
  • Deadline27 Dec 2024, 11:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Cargo Vehicle

አምቦ ዩኒቨርሰቲ በ2012 በጀት ዓመት የአይሱዙ የጭነት መኪና ስፖንዳ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Ambo University (የአምቦ ዩኒቨርሲቲ)


የጨረታ  ማስታወቂያ

 

አምቦ ዩኒቨርሰቲ በ2012 በጀት ዓመት የአይሱዙ የጭነት መኪና ስፖንዳ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆንም በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራች መሳተፍ ይችላል።

  1. ለሽያጭ የቀረበው የአይሱዙ ስፖንዳ ዝርዝር ሁኔታ ፡-
    • አይሱዙ የጭነት መኪና ሻንሲ ቁጥር ፡- JAANPR 71HH71011765
    • የመጫን አቅሙ - NPR በ35 ኩንታል
    • ያገልግሎት ሁኔታ በጣም ትንሽ ጊዜ ያገለገለ
    • የጨረታ መነሻ ዋጋ:- ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/
    • ስፖንዳው የሚገኝበት ቦታ፡- ዓለም ገና ካኪ አ/ማ ካምፓኒ ግቢ ውስጥ ስለሆነ በአካል በመገኘት መመልከት ይቻላል።
  2. የጨረታው ውጤት እንደታወቀ ለተሸናፊዎች የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ 10,000.00 ብር /አስር ሺህ ብር/ በሲፒኦ አሰርተው ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ሥርዝ ድልዝ ሳይኖረው 15% VAT በማካተት በጥንቃቄ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች በሌሎች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም፡፡
  5. ተጫራቾች ፋይናንሻል /ዋጋ ማቅረቢያ/ ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ በተለያየ ፖስታ ታሽጐ መቅረብ አለበት፤ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ለብቻው በታሸገ ፖስታ መቅረብ አለበት፤
  6. የጨረታ የመዝጊያው ቀን ማስታወቂያው ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛ ቀን ድረስ ሆኖ 15ኛው ቀን የበዓል ቀን ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ላይ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
  7. ተጫራቾች ዋጋ የሞሉበትን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ /ኤንቨሎፕ/ አድርገው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታተመበት የመጀመሪያው ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛ ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ድረስ አምቦ ዩኒቨርሲቲ የግዥ ዳይሬከቶሬት ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በ15ኛ ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ ዕለት በ5፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  8. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፉበትን ዋጋ አሸናፊ መሆኑ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ቀን ክፍያውን በማጠናቀቅ ስፖንዳውን ካለበት ቦታ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ማንሳት ይኖርበታል፡፡
  9. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልጋቸው በስልክ ቁጥር 011-2-363825 ወይም 0112609324 ደውለው ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  10. ዩኒቨርሲቲው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የአምቦ  ዩኒቨርሲቲ

 

Save Tender