Tender Detail

Tender Details

  • Deadline20 Dec 2024, 9:45 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Home Appliance And Supplies

በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅ/ጽ/ ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መ/ጣቢያዎች ተይዘው እና ተወርሰው የሚገኙ የሞተር ሳይክል እና የተሽከሪካሪ መለዋወጫዎች፣ አልባሳት ዕቃዎች ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የሞባይል ቀፎዎች፣ ኮስሞቲክስ እና የንፅጽና መጠበቂያ ዕቃዎች፣ የቤት  ውስጥ መገልገያ እና ማስዋቢያ ዕቃዎች ሞተርሳይክሎች ብዛቱ 64 ካርቶን እያንዳንዱን ካርቶን በቁጥር 10,000 ቆርኪ (CROWN CORKE እና ነዳጅ እንዲሁም ሌሎች ዕቃዎች በግልጽ እና በሃራጅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


የጨረታ  ሽያጭ  ማስታወቂያ  የጨረታ ቁጥር 11/2017

 

በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅ/ጽ/ ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መ/ጣቢያዎች ተይዘው እና ተወርሰው የሚገኙ የሞተር ሳይክል እና የተሽከሪካሪ መለዋወጫዎች፣ አልባሳት ዕቃዎች ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የሞባይል ቀፎዎች፣ ኮስሞቲክስ እና የንፅጽና መጠበቂያ ዕቃዎች፣ የቤት  ውስጥ መገልገያ እና ማስዋቢያ ዕቃዎች ሞተርሳይክሎች ብዛቱ 64 ካርቶን እያንዳንዱን ካርቶን በቁጥር 10,000 ቆርኪ (CROWN CORKE እና ነዳጅ እንዲሁም ሌሎች ዕቃዎች በግልጽ እና በሃራጅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ቅድመ ሁኔታዎች እና መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃዎች ጋር ተዛማችነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና መለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  2. ተጫራቾች የግልጽ ጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00- 12:00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በጽ/ቤታችን የእለት ገቢ ገንዘብ ሰብሳቢ ቢሮ ቁጥር 16 በመገኘት የጨረታ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ መዝጊያ ቀን ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  3. በግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና (CPO) እንዲሁም በሃራጅ ጨረታ የሚቀርቡ እቃዎችንም በተመለከተ የመግዣ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) በጉምሩከ ኮሚሽን በሞያሌ ቅርንጫፍ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  4. ጨረታው የሚካሄደው በሞያሌ ቅጽ/ቤት ሲሆን ተጫራቾች (ህጋዊ ወከሎቻቸው) ባሉበት ወይም ታዛቢ ፊት ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች ማስታወቂያ በጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር እስከ 7ኛው ቀን ድረስ ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች ናሙና በሞያሌ እና በሁሉም መ/ጣቢያ የሚገኙ መጋዝኖቻችን እየሄዱ መመልከት አለባቸው።
  6. በጨረታው የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር በ8ኛው ቀን ሲሆን ጨረታው ከጠዋቱ 3፡45 (ሶስት ሰዓት ከአርባ አምስት ደቅቃ) ተዝግቶ 4፡00 (አራት ሰዓት) ላይ ይከፈታል።
  7. ከላይ በተራ ቁጥር 6 በተገለጸው ጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 8ኛው ቀን ስራ ቀን ሳይሆን ሲቀር ጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
  8. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታውን ውጤት ከተገለጸ በ 3 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  9. አሽናፊ ተጫራች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ 5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ከላይ በተራ ቁጥር 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት CPO ለመ/ቤቱ ግቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
  11. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው -

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0464441415 /0464441564 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ

 

በኢትዮጵያ  ጉምሩክ  ኮሚሽን  የሞያሌ  ቅርንጫፍ  ጽ/ቤት

Save Tender