Tender Detail

Tender Details

  • Deadline19 Dec 2024, 9:45 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Home Appliance And Supplies

በጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ አልባሳት፣ ኮንስትራክሽን፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት እቃ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ ጫማዎች፣ ምግብ ነክ፣ ለስፔርፓርት የጽዳት እቃ እና ልዩ ልዩ በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


የግልፅ  እና  የሀራጅ  ጨረታ  ማስታወቂያ

 

በጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ አልባሳት፣ ኮንስትራክሽን፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት እቃ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ ጫማዎች፣ ምግብ ነክ፣ ለስፔርፓርት የጽዳት እቃ እና ልዩ ልዩ በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን እቃዎች በቀን 08/04/2017 ጀምሮ ሳምፕል በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መመዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል፡፡

ስለሆነም  በጨረታው  ላይ  ለመካፈል  የምትፈልጉ  ተጫራቾች

  1. ለግልፅ እና ለሀራጅ ጨረታ በዘርፍ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተስጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፤
  2. በሀራጅ ጨረታ ለመሳተፍ እቃውን ለመግዛት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ማቅረብ የሚችል፤
  3. በግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ እቃውን ለመግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ማቅረብ የሚችል፤
  4. ለሃራጅ ጨረታ ተጫራቹ የሚገዛበትን መነሻ ዋጋ እራሱ ያቀርባል፤
  5. ለግልፅ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤
  6. ተጫራቹ በጨረታው አሸንፎ የገዛውን እቃዎች ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ የሚረከብ መሆን አለበት፤
  7. እቃዎቹን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ለመንግስት ገቢ ይሆናል፤
  8. በጨረታው ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
  9. አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል፤
  10. ማንኛውም ተጫራች እቃዎቹን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየቦታው ርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል።
  11. ተጫራቹ እቃዎቹን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም፡፡
  12. ተጫራቾች የሞሉትን የግልጽ ጨረታ ሰነድ በቀን 10/04/2017 ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 3:45 በጅግጅጋ ጉ/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው 3:45 ተዘግቶ በቀን 10/04/2017 ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል
  13. የሀራጅ ጨረታው የሚካሄደው በቀን 10/04/2017 ከረፋዱ 4:15 በቅ/ጽ/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፤

NB- አሸናፊው ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት) የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፤ ሳምፕል ሳያዩ ለሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም።

 

በጉምሩክ  ኮሚሽን  ጅግጅጋ  ቅ/ጽ/ቤት

Save Tender