በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ከ2017 በጀት ዓመት ጀምሮ ለአንድ ዓመት የሆቴል አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Addis Ababa Driver and Vehicle Licensing and Control Authority (በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር :- አሽተሽፍቁባ /መግዳ/ 2017/ 001
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ከ2017 በጀት ዓመት ጀምሮ ለአንድ ዓመት የሆቴል አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
-
- ንግድ ምዝገባ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት (ቲን ነምበር)፣ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ክሊራንስ፣ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባችሁ፡፡
- ማስታወቂያው አየር ላይ የሚቆየው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ እለት ከጧቱ በ4፡30 ሰዓት መከሊት ሕንፃ 8ኛ ፎቅ ከሚገኘው ትልቁ የስብሰባ አዳራሽ (806) ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን 22 መከሊት ሕንፃ 8ኛ ፎቅ ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 804 ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ድረስ በማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመግዛት መውሰድ ትችላላችሁ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያነት፡- ለሆቴል መስተንግዶ አገልግሎቶች የ30,000.00 ብር (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ ሲፒኦ (CPO) አሰርታችሁ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡
- የተጫራቾች የሆቴል ደረጃ ባለ 4 ኮከብና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርበታል፡፡
- ሆቴሉን ለቴክኒከ ኮሚቴዎች ማሳየት አለባችሁ፡፡
- ባለስልጣን መስሪያቤታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ውይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አድራሻ:- ከጐላጐል ታወር ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ መክሊት ሕንፃ 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 708፤ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-6-67-23-36 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን
