ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን የአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት ደረጃ GC/BC-9 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የግንባታ ሥራ ማህበራትን ሥራ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ በአለም ገበያ ከተማ ውስጥ የማህበረሰብ ፋርማሲ የግንባታ ሥራ ለማሰራት ይፈልጋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን የአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን የአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት ደረጃ GC/BC-9 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የግንባታ ሥራ ማህበራትን ሥራ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ በአለም ገበያ ከተማ ውስጥ የማህበረሰብ ፋርማሲ የግንባታ ሥራ ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ለስራው ብቁ የሆኑ ሆኑ ተጫራቾች የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ከግብር እዳ ነፃ ስለመሆናቸው እንዲሁም የመንግሥት መስሪያ ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የሥራ ቀናት የአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በመምጣት ለጨረታ ሰነድ የማይመለስ 300 /ሦስት መቶ/ ብር መክፈል መግዛት ይችላሉ።
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 /ሃያ ሺህ/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
ከማንኛውም ኢንሹራንስ እና ከባንከ የሚቀርብ ሁኔታዊ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት ፋይናንሻልያና ቴክኒካል ዶክንቱን በሚገባ በመሙላት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ቅጂ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ ታህሣሥ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ በአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ታህሣሥ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዛው እለት 9፡30 ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡-
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ በሙሉ የመሰረዝ በህግ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የተወዳዳሪ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታውን መክፈቻ ቀን አይለውጥም።
- ለበለጠ መረጃ፡-ስልክ ቁጥር 0911769699 ወይም 0912719762 ይደውሉ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን የአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት
