Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address ሀዋሳ ከተማ ፔፕሲ ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የሐዋሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት አዲሱ የውርስ መጋዘን ቅጥር ግቢ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0462125896
  • Website
  • Deadline16 Dec 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Textile, Garment & Leather

የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የተተውና ተወርሰው የሚገኙ መገናኛ መሣሪያዎች፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ አልባሳትና ጨርቃጨርቅ፣ የመኪና መለዋወጫ፣ መዋቢያና የንፅህና መጠበቂያዎች፣ ያገለገሉ ሞተር ሣይከሎች እና ምግብ ነክ በግልፅና በሃራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


 

የጨረታ  ማስታወቂያ  ቁጥር  24/2017

በጉምሩክ  ኮሚሽን  የሀዋሳ  ቅ/ጽ/ቤት  የተተውና  የተወረሱ  ዕቃዎች  ሽያጭ

 

የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የተተውና ተወርሰው የሚገኙ መገናኛ መሣሪያዎች፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ አልባሳትና ጨርቃጨርቅ፣ የመኪና መለዋወጫ፣ መዋቢያና የንፅህና መጠበቂያዎች፣ ያገለገሉ ሞተር ሣይክሎች እና ምግብ ነክ በግልፅና በሃራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  1. ማንኛውም ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል። ግምታዊ ዋጋው ከብር 500 ሺህ በታች የሆነውን ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም።
  2. ማንኛውም የሞተር ሣይከል ተጫራች ዕድሜው 18 ዓመት የሞላው ኢትዮጵያዊ መታወቂያ በማቅረብ መጫረት ይችላል።
  3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ከሰዓት ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት፣ ቅዳሜ ከ 2፡00 እስከ-6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በተጫራቹ ስም የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ ከገቢ ሂሳብና ዋስትና አስተዳደር ቡድን መውሰድ ይችላሉ።
  4. ማንኛውም የግልፅ ጨረታ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን C.P.O፣ የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
  5. ማንኛውም የሃራጅ ጨረታ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን ለመገናኛ መሣሪያ 500 (አምስት መቶ ሺህ ብር) ለኤሌከትሪክ ዕቃዎች 50,000 (ሃምሣ ሺህ ብር) ለአልባሳትና ጨርቃ ጨርቅ ለእያንዳንዱ ኮድ 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር)፣ ለመኪና መለዋወጫ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ለመዋቢያና ለንፅህና መጠበቂያ 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) እና ላገለገሉ ሞተር ሣይከሎች ለእያንዳንዱ ኮድ 50,000 (ሃምሣ ሺህ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን C.P.O የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርበታል።
  6. ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 5ኛው (አምስተኛው) ቀን ድረስ የንብረቶቹን ናሙና በመደበኛ የስራ ሰዓት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ማየት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ6ኛው (ስድስተኛው) ቀን ግልፅ ጨረታው ጠዋት 4፡00 ሰዓት በአዲሱ መጋዘን ይካሄዳል። የሃራጅ ጨረታው የግልፅ ጨረታው ከተጠናቀቀ ከ10 ደቂቃ በኋላ ይካሄዳል። ነገር ግን የጨረታው ቀን እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከዋለ በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የስራ ቀን ይካሄዳል።
  7. ማንኛውም የግልፅና የሃራጅ ጨረታ ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የሰጠውን ዋጋና መግለጫ መለወጥ እና ማሻሻል አይችልም።
  8. ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ ቅ/ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
  9. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም።
  10. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በዕለቱ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ግን ከሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል።
  11. ተጫራቾች ዕቃውን ሳያዩ ዋጋ ቢሰጡና ችግር ቢፈጠር ቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።
  12. ለጨረታው የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ ነው::
  13. አሽናፊው ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል። ይህንን ባያደርጉ ጨረታው ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሚ በጨረታ ላይ ይወጣል።
  14. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ  መረጃ  የስልክ  ቁጥር ፡- 0462125396

 

በጉምሩክ  ኮሚሽን  የሀዋሳ  ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender