ድርጅታችን ነገም ሌላ ቀን ነው ከኤች አይ ቪ/ኤድስ ጋር የሚኖሩ ሴቶች ድጋፍ ሰጪ ድርጅት እ.ኤ.አ በ2024 በጀት አመት ሂሳቡን በተመሰከረላቸው ኦዲተሮች ማስመርመር ይፈልጋል።
ነገም ሌላ ቀን ነው ከኤች አይ ቪ/ኤድስ ጋር የሚኖሩ ሴቶች ድጋፍ ሰጪ ድርጅት
የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ነገም ሌላ ቀን ነው ከኤች አይ ቪ/ኤድስ ጋር የሚኖሩ ሴቶች ድጋፍ ሰጪ ድርጅት እ.ኤ.አ በ2024 በጀት አመት ሂሳቡን በተመሰከረላቸው ኦዲተሮች ማስመርመር ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሰውን መስፈርት የምታሟሉና ሥራውን መሥራት የምትፈልጉ የኦዲት ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከህዳር 29 ቀን 2017 ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዱ በማስገባት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
መሟላት ያለባቸው ሰነዶችና መስፈርቶች ፡-
- የኦዲት ሥራ ህጋዊ ፈቃድ ለ2017 ዓ.ም የታደሰ
- የሙያ ማረጋገጫ ፈቃድ ያለው
- በኦዲት ሥራው ላይ የስምንት አመት ልምድ ያለው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin number) ያለው
- የኦዲት ሥራውን የሚያጠናቅቁበትና ሪፓርቱን የሚያስረክቡበት ጊዜ ገደብ
- የኦዲት ሥራውን ለመሥራት የሚያስከፍለው ገንዘብ መጠን (Audit fee)
- ሰርቶ የሚያጠናቅቅበት ጊዜ
የድርጅቱ አድራሻ አዲስ አበባ ጉለሌ ወደ ሸጎሌ በሚወስደው መንገድ ከነማ ፋርማሲ ዋና መስሪያቤት ከፍ ብሎ ምህረት ክሊኒክ የሚገኝበት ሰማያዊ ህንጻ ሁለተኛ ፎቅ፤
የመልእክት ሳጥን ቁጥር 59611
ስልክ ቁጥር 0112-592476/0911667082/0911345348/0900762146
