Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዋና ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት የንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን
  • Address መድኃኒዓለም ከራስ ኃይሉ መዝናኛ ማዕከል አጠገብ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ህንፃ ዋና ስራ አስፈፃሚ ግዥ ቡድን 7ኛ ፎቅ በግራ ክንፍ በኩል ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 8 69 38 76
  • Website
  • Deadline21 Dec 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Wood And Wood Working

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት የንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን የተለያዩ ያገለገሉ የፈርኒቸር ውጤቶች ባለበት ሁኔታ የተለያዩ የተሰባበሩ መንበሮች የተለያዩ የተሰባበሩ የእንጨት ሼልፎች፣ የተለያዩ የተሰባበሩ ግሩፕ ጠረጴዛዎች እና የተለያዩ የተሰባበሩ የእንጨት ፋይል ካቢኔቶች ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዋና ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት የንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ  ቁጥር  01/2017 ዓ.ም

 

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት የንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን የተለያዩ ያገለገሉ የፈርኒቸር ውጤቶች ባለበት ሁኔታ የተለያዩ የተሰባበሩ መንበሮች የተለያዩ የተሰባበሩ የእንጨት ሼልፎች፣ የተለያዩ የተሰባበሩ ግሩፕ ጠረጴዛዎች እና የተለያዩ የተሰባበሩ የእንጨት ፋይል ካቢኔቶች ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም  ተጫራቾች  ከዚህ  በታች  የተመለከተውን  ነጥቦች  በማሟላት  ቀርበው  መወዳደር  ይችላሉ፡፡

  1. በግልጽ ጨረታው በቀረበው ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የተለያዩ ያገለገሉ የፈርኒቸር ውጤቶች ባለበት ሁኔታ የተለያዩ የተሰባበሩ ወንበሮች ፣ የተለያዩ የተሰባበሩ የእንጨት ሼልፎች፣ የተለያዩ የተሰባበሩ ግሩፕ ጠረጴዛዎች እና የተለያዩ የተሰባበሩ የእንጨት ፋይል ካቢኔቶች ባለበት ሁኔታ::
  2. በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህንፃ 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 704 በግራ ክንፍ በኩል የዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ከፍያና ሂሳብ ቡድን በመምጣት የንብረቱን ዝርዝር መመሪያ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ሰነድ ግዥ ይመለስልኝ የማትሉት ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ንብረቱን ከላይ በተጠቀሰው መ/ቤት በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በአሃዝ እና በፊደል በሰጠው ዋጋ ልዩነት ካለው ከፍተኛ ዋጋ በመውሰድ ያወዳድራል፡፡
  5. ተጫራቾች የሚገዙትን ዕቃዎች የጨረታ መነሻ ዋጋ 10 በመቶ(10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ ቤት ግዥ ቡድን 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 702 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር የስራ ቀናትን ከሰኞ እስከ ዓርብ ያሉ ቀናቶችን ታሳቢ በማድረግ በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾችን ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት የንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን ቢሮ ላይ ይከፈታል። ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታው መክፈት አያስተጓጉልም።
  7. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ7 /ሰባት/ የስራ ቀናት ውስጥ ቀሪ ክፍያውን በማጠናቀቅ የአሸነፈበትን ንብረት በ5 /አምስት/ የስራ ቀናት ውስጥ ማንሳት ይኖርበታል፡፡ የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋ እና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለፁትን አሟልቶ መገኘት አለበት፡፡
  8. የንብረቶቹ የጠቅላላ የመነሻ ዋጋ 10 በመቶ (10%) ያልያስያዘ እና በሰነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦች ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡
  9.  አሸናፊ የሚለየው በጥቅል ለተመደበው ዕቃዎች ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ይሆናል እና ከጨረታ መነሻ ዋጋ በታች እና መነሻ ዋጋ ሞልቶ ያቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
  10. የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ውጪ ከሆነ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  11. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸው ንብረቶች ሙሉ ክፍያ ከፍሎ እስከሚወስድ ድረስ ለውል አስተገባበር ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ (10%) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለበት፡፡
  12. አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረታቸውን በ5 /አምስት/ ቀናት ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡
  13. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011 8 69 38 76 ወይም 0118 96 17 50 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  14. በመ/ቤቱ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ ፡- መድኃኒዓለም ከራስ ኃይሉ መዝናኛ ማዕከል አጠገብ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ህንፃ ዋና ስራ አስፈፃሚ ግዥ ቡድን 7ኛ ፎቅ በግራ ክንፍ በኩል

 

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዋና ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት የንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን

Save Tender