Tender Detail

Tender Details

  • Company ቱምሣ ዴቬሎፕመንት ግሩፕ
  • Address ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 10ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-113-52-75
  • Website
  • Deadline20 Dec 2024, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Used Items

ቱምሳ ዴቬሎፕመንት ግሩፕ ያገለገሉ ሙሉ የወተት ማቀነባበሪያ ማሽን ዕቃዎችን በጨረታ ለማስወገድ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን ፡

ቱምሣ ዴቬሎፕመንት ግሩፕ


የጨረታ ማስታወቂያ

 

ቱምሳ ዴቬሎፕመንት ግሩፕ ያገለገሉ ሙሉ የወተት ማቀነባበሪያ ማሽን ዕቃዎችን በጨረታ ለማስወገድ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን ፡

  1. ኢትዮጵያዊ የሆነ እና የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ወይም ያላት፤
  2. የንግድ ፍቃድ ያለው፤ የዓመቱን ግብር የገበረ እንዲሁም በዲዬሪ ፋርም በመሰማራት የእቃውን ጥራት ተረድቶ ተገቢ ዋጋ መስጠት የሚችል፤
  3. ማንኛውም ተወዳዳሪ ተጫራች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንፃ 10ኛ ፎቅ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 11፡00 በመምጣት የማይመለስ 500 (አምስት መቶ) ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች በገዛው የጨረታ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም ወይም በመፈረም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የማሽኑን /ፋብሪካውን  አጠቃላይ መነሻ ዋጋ 10% በሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የሞሉትን ጨረታ ሰነድ አሪጅናል እና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በአንድ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተወዳዳሪዎች የገዙትን ሰነድ እና ደረሰኝ በመያዝ ያገለገሉ የማሽኑን/ ፋብሪካውን ሰበታ ክ/ከ በሚገኘው በድርጅቱ ፋብሪካ ግቢ ውስጥ በሥራ ሰዓት ማየት የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  7. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ የጨረታ መግቢያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሻያ ማድረግ እና እራሳቸውን ከጨረታ ማግለል አይችሉም
  8. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀናት አየር ላይ የሚውል ሆኖ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት 8፡30 ላይ ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  9. የጨረታ መክፈቻ ቀናት ፤ ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  10. የጨረታው አሸናፊ ከተረጋገጠ ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት የዋጋውን ውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ ውል መፈረም ይኖርበታል፡፡
  11. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ ፡- ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 10ኛ ፎቅ

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር ፡- 011-113-52-75

 

ቱምሣ ዴቬሎኘመንት ግሩኘ

Save Tender