ኢትዮ ቴሌኮም አዳዲስ እና ከአገልግሎት የተመለሱ የተለያዩ የሞባይል እና መደበኛ ስልክ ቀፎዎች፣ የተለያዩ የኔትዎርከ እና የፖወር ዕቃዎች፣ ያገለገሉ ባትሪዎች ቁርጥራጭ ፒቪሲዎች፣ የእንጨት ፖሎች፣ያገለገሉ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ ያገለገሉ የተሸከርካሪ የወንበር ልብሶች፣ ምንጣፎች፣ እና ጐማዎች፣ ቁርጥራጭ የኤችድፒ ዳክቶች፣ ያገለገሉ የኘሪንተር ቶነሮች፣ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ የተለያዩ የፍሎረሰንት ማቀፊያዎች እና ኤልኢዲ መብራቶች፣ ያገለገሉ የእሳት ማጥፊያዎች፣ ያገለገሉ የቢሮ ፈርኒቸሮች፣ የኢንፎርሜሽን ሲስተም ዕቃዎች፣ ቁርጥራጭ ካርቶኖች እና ወረቀቶች፣ የእንጨት ማሸጊያ ሳጥኖች፣ አጣናዎች እና ፓሌቶችን፣ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
Ethio Telecom (ኢትዮ ቴሌኮም)
የጨረታ ማስታወቂያ SC/L/WRM/001/2017
ኢትዮ ቴሌኮም አዳዲስ እና ከአገልግሎት የተመለሱ የተለያዩ የሞባይል እና መደበኛ ስልክ ቀፎዎች፣ የተለያዩ የኔትዎርከ እና የፖወር ዕቃዎች፣ ያገለገሉ ባትሪዎች ቁርጥራጭ ፒቪሲዎች፣ የእንጨት ፖሎች፣ ያገለገሉ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ ያገለገሉ የተሸከርካሪ የወንበር ልብሶች፣ ምንጣፎች፣ እና ጐማዎች፣ ቁርጥራጭ የኤችድፒ ዳክቶች፣ ያገለገሉ የኘሪንተር ቶነሮች፣ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ የተለያዩ የፍሎረሰንት ማቀፊያዎች እና ኤልኢዲ መብራቶች፣ ያገለገሉ የእሳት ማጥፊያዎች፣ ያገለገሉ የቢሮ ፈርኒቸሮች፣ የኢንፎርሜሽን ሲስተም ዕቃዎች፣ ቁርጥራጭ ካርቶኖች እና ወረቀቶች፣ የእንጨት ማሸጊያ ሳጥኖች፣ አጣናዎች እና ፓሌቶችን፣ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከህዳር 25 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ድረስ በማንኛውም ጊዜ እና ሰዓት ከextratenders.com፣ 2merkato.com እና afrotender.com ዌብ ሳይቶች በቴሌ ብር አማካኝነት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል እና በቀላሉ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ ሲሆን በተጨማሪም ንብረቶቹን መመልከት እንዲሁም ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የምትፈልጉ ተጫራቾች አዲስ አበባ በሚገኘው የኩባንያው ዕቃ ግምጃ ቤቶች (አቃቂ፣ መስቀል ፍላወር እና ገላን) የታደሰ መታወቂያችሁን በመያዝ መጎብኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ አቃቂ በሚገኘው የኩባንያው ዕቃ ግምጃ ቤት ታህሳስ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
ኩባንያው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም
