ማኅቶት ኮንስትራክሽን የሶስት (3) ዓመታትን ማለትም ከ2017 ዓ.ም እስከ 2019 ዓ.ም ሒሳቡን በተመሠከረላቸው መርማሪዎች (Certified Auditors) እና ዓለምአቀፍ ደረጃውን በጠበቀ ምርመራ ማስመርመር ይፈልጋል።
የማኅቶት ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ
የኦዲት ሥራ ጨረታ ማስታወቂያ
ማኅቶት ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ በ2009 ዓ.ም የተመሠረተና በዛ ባሉ የሥራ ዘርፎች ላይ ለመሰማራትና በሀገራዊ ግንባታ ላይ ድርሻውን ለመወጣት ዓላማ ሰንቆ የተመሠረተ ሲሆን መነሻ ያደረገውና ላለፉት ዓመታት ተሠማርቶ ያለበት በትምህርት ዘርፍ ላይ የሆነ አክስዮን ማኅበር ነው። ማኅበራችን ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ዓመታዊ የሒሳብ ምርመራውን በተመሠከረላቸው የውጪ ሒሳብ መርማሪዎች እያስመረመረ ቆይቷል።
በዚሁም መሠረት የሶስት (3) ዓመታትን ማለትም ከ2017 ዓ.ም እስከ 2019 ዓ.ም ሒሳቡን በተመሠከረላቸው መርማሪዎች (Certified Auditors) እና ዓለምአቀፍ ደረጃውን በጠበቀ ምርመራ ማስመርመር ይፈልጋል።
በዚህም መሠረት ፈቃደኛ የሆነ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ ድርጅት በጨረታው አግባብነት ካላቸው መረጃዎች ጋር በማያያዝ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
አድራሻ ፡- ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 (ጉርድ ሾላ)
ስልክ ቁጥር ፡- 0913985306/ 0913034772/0910101486
የማኅቶት ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ
የዳይሬክተሮች ቦርድ
