Tender Detail

Tender Details

  • Company በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ
  • Address ሚዛን አማን : ደቡብ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0471355629
  • Website
  • Deadline22 Dec 2024, 2:30 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Building Construction

በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት በሎት 1፡- የአሮጌ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታ ሎት ፡-2 የመስከረም ሲሲ ት/ቤት አንድ ብሎክ 4 የመማርያ ክፍል ግንባታ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል።

በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ


የጨረታ ማስታወቂያ

 

በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት በሎት 1፡- የአሮጌ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታ ሎት ፡-2 የመስከረም ሲሲ ት/ቤት አንድ ብሎክ 4 የመማርያ ክፍል ግንባታ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  1. ተጫራቾች በግንባታ ዘርፍ BC/GC -5 (አምስት) እና ከዚያ በላይ የሆነ
  2. የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
  3. ለበጀት ዓመቱ የሚያገለግል የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
  4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin no) ያላቸው፤
  5. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣
  6. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው፣
  7. ተጫራቾች ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ብር 130,000 /አንድ መቶ ሰላሳ ሺህ/ ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ፤ በባንክ በተረጋገጠ ጋራንቲ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ ሌተር ኦፍ ክሬዲት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምርያ በማለት ማሰራት ይኖርባቸዋል።
  8. ተጫራቾች ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከመምሪያው የግዥና ንብረት አስ/ር ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 100 መግዛት ይችላሉ።
  9. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ሃሳብ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል አንድ አርጅናል እና ሁለት ኮፒ እያንዳንዱ ለየብቻ በማሸግ እና በጥቅል በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ መቅረብ አለበት፤
  10. ተጫራቾች በየአንዳንዱ በሰም ታሽጎ ማህተም በመምታት ሙሉ አድራሻ በመፃፍ እና በመፈረም ኦርጅናል እና ኮፒ የሚል ጽሁፋ በማለት ተፈርሞበት በጥንቃቄ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በታሸገ ኤንቨሎፕ በጨረታ ማስታወቂያው ከተመለከተው የጊዜ ገደብ በፊት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ፣ የግዥና ንብረት አስ/ር ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 100 ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ገቢ መደረግ አለበት።
  11. ጨረታው ማስታወቂያ በወጣው 21ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ታሽጎ በዚያው ቀን በ9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።

ማሳሰቢያ፣

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት በሚመጡበት ግዜ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የዘመኑ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ቫት ተመዝጋቢ ሰርተፍኬት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የማይመለስ ኮፒ ይዘው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል

መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡- 0471355629

 

የቤንች ሸኮ ዞን ፋይ/ኢኮ/ል/ መምሪያ፣ ሚዛን አማን

Save Tender