የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ መድሃኒትና ሌሎች የህክምና ግብአቶችን ለማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥውን ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
Hawassa University College of Medicine and Health Sciences (የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ)
የግዥ መለያ ቁጥር ፤ HU/CMHS/NCB/Medicine &
Others/05/05/2017 BY
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ መድሃኒትና ሌሎች የህክምና ግብአቶችን ለማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥውን ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ከፌደራል ሀገር ውስጥ ገቢ ወይንም ከሌሎች ግብር ሰብሳቢ የመንግስት መ/ቤቶች ወቅታዊ የግብር ግዴታቸውን የተወጡና በመንግስት ጨረታዎች መካፈል የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ፣ በፌደራል ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የመረጃ መረብ ድረ-ገጽ /web-site/ ላይ የተመዘገቡ እና የሚጫረቱበት ዋጋ ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ የሚበልጥ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም CPO ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 250.00 (ሁለት መቶ ሀምሳ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሠነድ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግዥ ሥራ አስፈጻሚ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ ብቻ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ታህሳስ 08 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ በኮሌጁ ግዥ ሥራ አስፈጻሚ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ታህሳስ 08 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 8፡40 ሰዓት ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
ስልክ 251-462-12-01-20
ፋክስ 251-462-20-87-55
