የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ከአላጌ የግብርና ማሰልጠኛ ተቋም ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ Distribution board; socket and switch ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር DCE/EM/146/2024
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ከአላጌ የግብርና ማሰልጠኛ ተቋም ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ Distribution board; socket and switch ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
No |
የዕቃው ዓይነት |
ፕሮጀክት |
የጨረታ ቁጥር |
የጨረታው መዝጊያ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ ማስከበሪያ ብር |
|
1 |
Distribution board socket and switch |
አላጌ የግብርና ማሰልጠኛ |
DCE/EM/146/2024 |
ታህሳስ 9/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 |
ታህሳስ 9/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 |
50000 ብር |
ስለሆነም ፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ፤ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ እና በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችላቸው ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ የታደሰ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ ቦንድ (Bid Bond) 120 ቀን ፀንቶ የሚቆይ ማቅረብ ይኖርበታል። የጨረታ ማስከበሪያው እንደ ተጫራቹ ምርጫ በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Gurantee) ወይም በባንክ የተሰጠ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ የመድን ድርጅቶች ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።
- አንድ ተጫራች መወዳደር የሚችለው በአንድ ዓይነት ምርት (ብራንድ) ብቻ ነው። በአማራጭ የቀረበ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ትምህርት ቤት አጠገብ (ቃሊቲ ቶታል አዲሱ ስታዲየም ጀርባ) አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋናው መ/ቤት ግዥ ቡደን ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነዱ በተያያዘው ዝርዝር እና ብዛት መሰረት መሆን ይኖርበታል።
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34
ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72
ፖ.ሳ.ቁ 3414 ፋክስ ቁ. 0114-40-04-71/0114-42-07-46
አድራሻ፡- በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ትምህርት ቤት
አጠገብ (ቃሊቲ ቶታል አዲሱ ስታዲየም ጀርባ) እንገኛለን።
ድህረ ገፅ - www.dce.et.com
ኢሜል ፡- INFO@dce-et.com
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
