Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ኮምቦልቻ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
  • Address ኮምቦልቻ ከተማ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 033-551-02-05
  • Website
  • Deadline14 Dec 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Used Items

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የኮምቦልቻ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ኮምቦልቻ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት


ግልፅ  የጨረታ  ማስታወቂያ

የጨረታ  ቁጥር  001/2017

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የኮምቦልቻ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም  ተጫራቾች  ከዚህ  በታች  የተጠቀሱትን  መስፈርቶች  በማሟላት  ቀርበው  መወዳደር  ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት (Tin Number) ያለው እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉበት መረጃ እና የታደሰ መታወቂያ በማቅረብ የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት የኮምቦልቻ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታው ሰነድ ውስጥ የተመለከቱትን መስፈርቶች አሟልቶ ከፍተኛ ዋጋ የሚያቀርብ ነው፡፡
  3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን አሟልቶ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ከተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚቻለው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ብቻ ነው፡፡
  4. ተጫራቾች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ሁሉንም መጫረት ግዴታ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በኢትዮጵያ መንገዶች ኣስተዳደር ሰነዳቸው የኮምቦልቻ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ስም አሰርተው በባንከ የተረጋገጠ (CPO) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ በ 4፡30 ሰዓት ኮምቦልቻ በሚገኘው በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የኮምቦልቻ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  7. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር 033 551 0205, 033 551 3002, 033 551 2268 ማግኘት ይችላሉ።

 

በኢትዮጵያ  መንገዶች  አስተዳደር  ኮምቦልቻ  መንገድ  ጥገና  ዲስትሪክት

Save Tender