በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የአብቹና ኘኣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለአብቹና = ኘኣ ወረዳ መንገድና ሎጅስቲክ ጽ/ቤት በወረዳ ውስጥ ለሚገኙ ለተለያዩ ቀበሌዎች የመንገድ ጥገና የሥራ ግንባታ ከቦጠራ ብለት እስከ አኖ አከብዶ 12.5km ፤ ከነስሪ ጥርኝ ድርማ 11.5 km እና ከጋዱላ ሞዬ አመንቴ ጎሮ ድረስ 6.1 km ለመንገድ ግንባታ የሚያስፈልጉትን ማሽኖችን ተከራይቶ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የአብቹና ፕአ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የአብቹና ኘኣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለአብቹና = ኘኣ ወረዳ መንገድና ሎጅስቲክ ጽ/ቤት በወረዳ ውስጥ ለሚገኙ ለተለያዩ ቀበሌዎች የመንገድ ጥገና የሥራ ግንባታ ከቦጠራ ብለት እስከ አኖ አከብዶ 12.5km ፤ ከነስሪ ጥርኝ ድርማ 11.5 km እና ከጋዱላ ሞዬ አመንቴ ጎሮ ድረስ 6.1 km ለመንገድ ግንባታ የሚያስፈልጉትን ማሽኖችን ተከራይቶ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት ፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ የማሽን ኪራይ ፈቃድ ያለውና የታደሰ የፒ.ኤል.ሲ(PLC) የንግድ ፈቃድ ያለው ሆኖ የዘመኑን ግብር የከፈሉ በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ለመሆኑ መረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ለመከፈሉ ከገቢዎች ደብዳቤ ማቅረብ አለበት፡፡
- የአቅራቢዎች ዝርዝር (Supply list) መረጃ ማቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከባንከ (Cpo) 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ለአብቹና ኘኣ ገንዘብ ጽ/ቤት የተፃፈውን አርጂናል የቴክኒክ ሰነድ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች የውል ማስከበሪያ (performance bond) 10% ከጠቅላላ ዋጋ ማስያዝ አለበት። አሸናፊ ተጫራች የጨረታ ውል ማስከበሪያ (Cpo) ያላቀረበ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ለመንግሥት ገቢ ሆኖ ሌላ ተጫራች እንዲያቀርብ ይደረጋል፡፡
- በጨረታ ሰነድ ላይ የተዘረዘሩትን ማሽኖች ሁሉ አንድ ላይ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት። ከፋፍሎ መወዳደር አይቻልም፡፡
- ፖስታው የሚቀርበው በተወዳዳሪ መመሪያ ላይ በተጻፈው ሁኔታ ተፅፎ መቅረብ አለበት፡፡
- የተወዳዳሪ ስም፤ የፕሮጀከት ባለቤት ስም፤ የፕሮጀክት ስም፤ የተወዳዳሪ ፊርማና ማህተም፤ የተወዳዳሪ አድራሻና የፕሮጀክት ባለቤት በፖስታ ላይ በግልፅ መፃፍ አለበት፡፡
- ለውድድር በቀረቡት ሰነዶች ሁሉ ላይ የድርጅቱ ሊቀመንበር ስምና ፊርማ እንዲሁም የድርጅቱ ማህተም በግልፅ መገኘት አለበት፡፡
- በሰነዱ ለይ ስረዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
- ማንኛውም ተወዳዳሪ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ሃሳብን መቀየር ወይም ማሻሻልና ከጨረታ ውስጥ እራሱን ማውጣት (ማግለል ) አይችልም። እንደዚሁም ማንኛውም ተወዳዳሪ ከተባለው ሰዓት ውጪ ሰነድ መግዛትም ሆነ መመለስ አይችልም፡፡
- ተወዳዳሪዎች ጨረታውን ለማጭበርበርም ሆነ ለማሳሳት ሙከራ ያደረገ ከጨረታ ይሠረሳል።
- ተወዳዳሪዎች በመንግስት ግዥ ቅጣት የሌላቸውና ያልተወገዱ መሆን አለባቸው፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ማሽኖችን ማቅረብ፤ ነዳጅና ትራንስፖርት እንዲሁም ከዚህ ጋር የተያያዙ ወጪዎችን እራሱ መሸፈን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከአብቹና ኘኣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ22ኛው ቀን ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው፤ የፕሮጀክት ኮሚቴዎችና የቴክኒክ ኮሚቴዎች በተገኙበት በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8፡30 በአብቹና ኘኣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የሚከፈት ሆኖ ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በቀጣዩ የሥራ ቀን በወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ ፡- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የቦታ ርቀት እየጨመረ ሲሄድ የአንዱን ባጆ ዋጋ ሲሞላ እየጨመረ ያልሄደ ድርጅት ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
አድራሻ ፡-
አብቹና ኘኣ በወረዳ መንዲዳ ከተማ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር:- 0913299765
በሰሜን ሸዋ ዞን የአብቹና ኘአ ሠረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
