የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ በ2017 በጀት አመት የሚገለገልባቸውን የተለያዩ አይነት የአገልግሎቶች እና የእቃ ግዥዎችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ከዚህ በፊት ግልፅ ጨረታ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም በመጀመሪያው ዙር ጨረታ ላይ በተለያዩ አሳማኝ ምክንያቶች ውድቅ የተደረጉ ጨረታዎችን በድጋሚ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍ ፈቃደኛ የሆናችሁ ተጫራቾች እንድትሳተፉ እየጋበዝን እቃዎቹ እና አገልግሎቶቹ እንደሚከተሉት ተዘርዝረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ፡- አ/አ/ከ/አስ/ምገባ ኤጀንሲ/ብ.ግ.ጨ/እ.ግ/03/2017 እና
አ/አ/ከ/አስ/ምገባ ኤጀንሲ/ብ.ግ.ጨ/አገ.ግ/04/2017
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ በ2017 በጀት አመት የሚገለገልባቸውን የተለያዩ አይነት የአገልግሎቶች እና የእቃ ግዥዎችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ከዚህ በፊት ግልፅ ጨረታ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም በመጀመሪያው ዙር ጨረታ ላይ በተለያዩ አሳማኝ ምክንያቶች ውድቅ የተደረጉ ጨረታዎችን በድጋሚ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍ ፈቃደኛ የሆናችሁ ተጫራቾች እንድትሳተፉ እየጋበዝን እቃዎቹ እና አገልግሎቶቹ እንደሚከተሉት ተዘርዝረዋል፡፡
|
ምድብ ቁጥር |
የሚገዛው እቃ /አገልግሎት/ አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ ብር |
|
ሎት 1 |
የሆቴል አገልግሎት ግዥ |
60,000 ብር |
|
ሎት 2 |
ለባህላዊ ምግብ አገልግሎት ግዥ |
30,000 ብር |
|
ሎት 3 |
ለተለያዩ የመስተንግዶ አገልግሎት ግዥ |
20,000 ብር |
|
ሎት 4 |
የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና አገልግሎት ግዥ |
10,000 ብር |
|
ሎት 5 |
የአጥር፤ የኤሌክትሪክ ጥገና እና የፓርቲሽን ስራ አገልግሎት ግዥ |
15,000 ብር |
|
ሎት 6 |
የፈርኒቸር እቃዎች እና ሌሎች የጥገና አገልግሎት ግዥ |
8,000 ብር |
|
ሎት 7 |
የመድረክ ዝግጅት አገልግሎት ግዥ |
12,500 ብር |
|
ሎት 8 |
የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ |
20,000 ብር |
|
ሎት 9 |
የስጦታ እቃዎች ግዥ |
6,000 ብር |
|
ሎት 10 |
የፈርኒቸር እና የብረት ካዝና ግዥ |
4,000 ብር |
|
ሎት 11 |
የወለል ምንጣፍ እና መጋረጃ ግዥ |
4,000 ብር |
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታከስ NAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የምትወስዱ መሆኑን እየገለፅን ይህ ጨረታ በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆናል፡፡
- የጨረታው ሰነድ መመለሻ የመጨረሻ ቀን በ30/03/2017 ዓ.ም 3፡30 ሰዓት ነው::
- ጨረታው በቀን 30/03/2017 ዓ.ም በ3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በቀን 30/03/2017 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ሌሎች መረጃዎችን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ኤጀንሲው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ፒያሳ ኤሊያና ሆቴል ፊት ለፊት (ዶን የጥርስ ህክምና) ያለበት ህንጻ ላይ 8ኛ ፎቅ ግዥና ንብረት ጠቅላላ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይገኛል፡፡
አድራሻ ፡- ፒያሳ ኤሊያና ህንጻ ፊት ለፊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቤተክህነት (ዶን የጥርስ ህክምና ያለበት) ህንጻ ላይ 8ኛ ፎቅ የግዥና ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክትሬት ቢሮ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር ፡- +251-1-18-12-83-21
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ
