በአብክመ የኦሮ ብ/ዞን የደዋ ጨፋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ/ን/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት በ2017 በጀት አመት በልማታዊ ሴፍትኔት ካፒታል በጀት በወረዳው ስር ለሚገኘት ለደ/ጨ/ወ/ግብርና ጽ/ቤት እና ለደ//ጨ/ወ/መስኖ እና ቆላማ አካ/ልማት ጽ/ቤት ለሚያስገነቡት የኮሚኔቲ ፖንድና መስኖ ካናል ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ ሎት1. ሲሚንቶ፤ ሎት2. የግንባታ ማቴሪያሎች (የፋብሪካ ውጤቶች) ሎት3. የውሃ ዕቃዎችና HDPE በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊዎች ለመግዛት ይፈልጋል::
በኦሮሞ ብ/ዞን ገንዘብ መምሪያ የደ/ጨ/ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫረቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን መስፈርቶቹም:
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የምዝገባ የምስከር ወረቀት (Tin No) አብረው ማያያዝ የሚችሉና
- ከ 200,000 ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ የያዘ ከኦሮ/ብ/ዞ/ደ/ጨ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ዕለት ጀምሮ ለ30 /ለሠላሳ/ ተከታታይ ቀናት ገዝተው በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ / ኢንቨሎፕ/ በማሸግ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ31ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጐ በዚሁ ቀን 4:40 ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እየገለጽን፤ ሆኖም የመክፈቻው ዕለት በዓላት ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀናት በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለሞሉት ለጠቅላላ የጨረታ መጠን ላይ 1%/ፐርሰንት/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንከ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት መረጃ ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ለበለጠ መረጃ የተጫራቾችን መመሪያ ላይ መረዳት ይቻላል፡፡ ወይም በስልከ ቁጥር 033554-0225/0294 መደወልና መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- አሸናፊዎች ያሸነፉትን እቃ ደዋ ጨፋ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ በጨረታ አሸናፊ የሆኑት ተጫራቾች ውል ካልገቡ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ በሙሉ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
በኦሮሞ ብ/ዞን ገንዘብ መምሪያ የደ/ጨ/ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት