የመንቆረር ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በአማራ ክልል በምስራቅ ጎጃም ዞን በደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር የሚገኝ መንግሥታዊ የሆነ የልማት ድርጅት ሲሆን ለጅ+7 ህንፃ የእንጨት በር አቅርቦትና ገጠማ፣ ለጅ+7 ህንፃ ፒ.ቪ.ሲ በር አቅርቦትና ገጠማ፣ የደ/ብርሃን ጠቅላላ ሆስፒታል የእንጨት በር አቅርቦትና ገጠማ፣ ለጅ+7 ህንፃ አልሙኒየም አቅርቦትና ገጠማ፣ ለጅ+7 ህንፃ ዋተር ፕሩፍ አቅርቦትና ስራ እና የማሽነሪና ተሽከርካሪ አገልግሎት የሚውል ጎማ ከዚህ በታች በተቀመጠው መሰረት ማሰራት መግዛት ይፈልጋል፡፡
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የመንቆረር ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በአማራ ክልል በምስራቅ ጎጃም ዞን በደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር የሚገኝ መንግሥታዊ የሆነ የልማት ድርጅት ሲሆን ለጅ+7 ህንፃ የእንጨት በር አቅርቦትና ገጠማ፣ ለጅ+7 ህንፃ ፒ.ቪ.ሲ በር አቅርቦትና ገጠማ፣ የደ/ብርሃን ጠቅላላ ሆስፒታል የእንጨት በር አቅርቦትና ገጠማ፣ ለጅ+7 ህንፃ አልሙኒየም አቅርቦትና ገጠማ፣ ለጅ+7 ህንፃ ዋተር ፕሩፍ አቅርቦትና ስራ እና የማሽነሪና ተሽከርካሪ አገልግሎት የሚውል ጎማ ከዚህ በታች በተቀመጠው መሰረት ማሰራት መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ምድብ 1 ለጅ+7 ህንፃ የእንጨት በር አቅርቦትና ገጠማ
- ምድብ 2 ለጅ+7 ህንፃ ፒ.ቪ.ሲ በር አቅርቦትና ገጠማ
- ምድብ 3 ለደ/ብርሃን ጠቅላላ ሆስፒታል የእንጨት በር አቅርቦትና ገጠማ
- ምድብ 4 ለጅ+7 ህንፃ አልሙኒየም አቅርቦትን ገጠማ
- ምድብ 5 ለጅ+7 ህንፃ ዋተር ፕሩፍ አቅርቦትና ስራ
- ምድብ 6 ለማሽነሪና ተሽከርካሪ አገልግሎት የሚውል ጎማ አቅርቦት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስቅረብ ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት ፡-
- ተጫራቾች የምትጫረቱበትን ሰነድ ያንዱን ዋጋ በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀናት በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 7 ማስገባት አለባችሁ፡፡
- ጨረታው የጨረታ ማስገቢያው በተጠናቀቀ በቀጣይ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ላይ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በበአላት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡ ሆኖም በራሳቸው ፈቃድ በመክፈቻው ቀን ባይገኙ የጨረታውን መከፈት አያግደውም፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የተመዘገበና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የነጋዴነት መለያ ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር የገበሩና የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ደ/ማርቆስ ከተማ በሚገኘው መንቆረር ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ቁጥር 11 ድረስ በመቅረብ ብር 200 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ከምድብ 1 እስከ 5 ላይ የሚወዳደሩ ተጫራቾች በተያያዘው ድሮይንግ መሰረት ሰርተው ማስረከብ አለባቸው፡፡
- በየምድባቸው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ፋይናንሻል ኦሪጅናል እና ኮፒ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በምድብ 6 ላይ የተወዳደሩ ተጫራቾች ያሸነፉትን ጎማ ኢንተርፕራይዙ ድረስ በራሱ ትራንስፖርት በማቅረብ ማስረከብ አለበት፡፡
- ከምድብ እስከ 5 ያሉ ዕቃዎችን በየፕሮጀክቱ በራሱ ትራንስፖርት በማቅረብ ሰርቶና ገጥሞ ማስረከብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠ/ዋጋ 2% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የሚያቀርባቸው እቃዎች እና ሥራ በባለሙያ ወይም ቴስት ተረጋግጦ ማለፍ አለበት፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በየምድባቸው በሎት ወይም በጥቅል ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ መሙያው ላይ በተቀመጠው ፎርም መሰረት በትክክል ከቫት በፊት፣ ቫት፣ ከቫት ጋር ለይቶ አለመሙላት ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ 10% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና፣ የመድን ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለበት፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀላቸው ባሉት 7 /ሰባት/ የስራ ቀናት ውስጥ ውል መያዝ አለባቸው፡፡
- ኢንተርፕራይዙ የተሻለ መንገድ ወይም አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ :- 0930958351 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
በምስ/ጎጃም ዞን በደ/ማ ከተማ/አስ መንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት
